ሆርሞናል መርፌ የእርግዝና መከላከያ፡ ከመደበኛ የእርግዝና መከላከያ የሚመደብ ሲሆን፡ እርግዝናን ለ 3 ወራቶች ይከላከላል፡፡
💡 ማወቅ ያለብሽ
⭐ (Perfect use) በየ 3 ወሩ በሰዓቱና በአግባቡ መርፌው ከተወሰደ 99% እርግዝናን ይከላከላል፡ በዓመት ውስጥ ከ 100 ሴት 1 ሴት መከላከያውን በትክክል እየተጠቀመች ልታረግዝ ትችላለች
⭐ (Typical use) በመደበኛ አጠቃቀም፡ 94% እርግዝናን ይከለከላል፡ በዓመት ውስጥ ከ 100 ሴት 6 ሴት መከላከያውን እየተጠቀመች ልታረግዝ ትችላለች
⭐ ለሌላ ህክምና የምትወስጃቸው መድሃኒቶች፡ መርፌውን እርግዝና የመከላከል አቅሙን #አይቀንሰውም
⭐ ቅመምነቱ ከሰውነትሽ እስኪወጣ፡ እርግዝናን እስከ አንድ አመት ያክል ሊከለክልሽ ይችላል፡ በቅርብ የመውለድ እቅድ ካለሽ መርፌው አይመከርም
⭐ ለምታጠባ እናት ከወለደች ከ6 ሳምንት ጀምሮ የእርግዝና መከላከያውን መጠቀም ይቻላል
⭐ አንዳንድ ሴት ላይ፡ ከዚህ በፊት የወር አበባ በብዛት መፍሰስ ወይም የወር አበባ በሚመጣበት ጊዜ ህመም ካለሽ መርፌውን መጠቀም ስትጀምሪ ሊቀንሰው ይችላል
⭐ የአባላዘር በሽታን፡ ኤች አይ ቪን ጨምሮ አይከላከልም
📌 አወሳሰዱ በህክምና ባለሙያ በመታገዝ በማንኛውም ሰዓት መርፌውን መወጋት ይቻላል፡ ነገር ግን ፔሬድ በመጣ የመጀመሪያ 5 ቀናቶች ከተወጋሽ፡ ምንም አይነት ተጨማሪ መከላከያ አያስፈልግሽም፡ ከነዚህ ቀናቶች ውጭ ከሆነና ግንኙነት ካለሽ፡ መርፌውን ከመውሰድሽ ከ 7 ቀን በፊት ኮንዶም ወይም ሌላ መከላከያ መጠቀም ይኖርብሻል፡፡
📌 የጎንዮሽ ጉዳቶች
👉 መርፌውን እየተጠቀምሽና ካቆምሽ በኋላ ለተወሰኑ ወራቶች የሚቆይ የወር አበባ መዛባት (በመሃል ደም መፍሰስ፡ በብዛት መፍሰስ፡ ለአጭር ጊዜ መፍሰስ፡ ፔሬድ ሳይመጣ ወሩን ማሳለፍ፡ ወይም ጭራሽ ለተወሰነ ጊዜ የወር አበባ መቅረት)
👉 እራስ ምታት
👉 ክብደት መጨመር
👉 የስሜት ወይም የባህሪ ለውጥ (mood swings)
👉 የጡት ህመም (breast tenderness)
👉 የራስ ጸጉር መነቃቀል/መሳሳት (hair loss)
👉 የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ
👉 ለረጅም ጊዜ ከተወሰደ የአጥንት መሳሳት ያስከትላል
📌 መርፌውን መጠቀም የማይመከረው መች ነው?
👉 መከላከያውን እንዳቆምሽ ቶሎ ወይም በ አንድ ዓመት ውስጥ ማርገዝ ካሰብሽ
👉 ምክንያቱ ያልታወቅ፡ በወር አበባ መሃል ደመ የሚፈስሽ ከሆነ ወይም ከግንኙነት በኋላ መድማት ካለሽ
👉 የሚታወቅ የስኳር በሽታ ካለሽ
👉 የሚታወቅ የልብ ህመም፤ የጉበት በሽታ ካለሽ
👉 የጡት ካንሰር ካለሽ ወይም ከዚህ በፊት ከነበረሽ
👉 የሚታወቅ migraine ካለሽ
Reviewed by Ayduwan
on
February 24, 2023
Rating:

No comments: