ስለ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ( Postpill ) ማወቅ ያለብሽ

 ስለ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ( Postpill ) ማወቅ ያለብሽ 


ደንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንደ ማንኛውም የእርግዝና መከላከያ፡ ያልታቀደ እርግዝናን ለመከላከል ይረዳል፡ ከመደብኛው የእርግዝና መከላከያ ለየት የሚያደርገው፡ ግንኙንት ካደረግሽ በኋላ መወሰዱ ነው፡፡ 

ከስሙ እንደሚያመላክተው ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ለድንገተኛ ጊዜ የምንጠቀመው የእርግዝና መከላክያ ሲሆን፡ መደበኛውን የእርግዝና መከላከያ አይተካም፡፡ መደበኛውን የእርግዝና መከላከያን መጠቀም የተሻለ እርግዝናን የመከላከልና ያነሰ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንዲኖር ይረዳል፡፡

❓ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ መቸ መጠቀም ይኖርብናል?

በአስገድዶ መደፈር ጊዜ፡ ኮንዶም ሲቀደድ ወይም በግንኙነት ጊዜ ሲወጣ፡ መደበኛ የእርግዝና መከላከያ ፒልስ አንድ ሁለት ቀን መውሰድ ከረሳሽ

🕒 አወሳሰዱ

ግንኙነት ባደረግሽ እስከ 72 ሰዓት በሉት ጊዜያቶች መውሰድ ትችያለሽ፡ ነገር ገን በ 12 ሰዓት ውስጥ ቶሎ መውሰድ መድሃኒቱ እርግዝናን የመከላከል እድሉን እንዲጨመር ያደርገዋል፡፡ 

⚠ መድሃኒቱን በምትወስጅበት ጊዜ የሚከሰቱ የጎንዮሽ ጉዳቶች

👉 ማቅለሽለሽ፡ ማስታውክ፡ ድካም፡ እራስ ምታት፡ የጡት መወጠር ህመም  

👉 የወር አበባ መዛባት፡ ከመደበኛው ቀን ቶሎ ወይም ዘግይቶ መምጣት፡ ብዛት ያለው ወይም ያነሰ የወር አበባ እንዲፈስሽ ያደርጋል፡

👉 መድሃኒቱ ከተወሰደ በኋላ ለአንድ ለሁለት ቀን የሚቆይ መጠኑ ትንሽ ደም መፍሰስ (spotting) 

👉 ከእምብርት በታች ቁርጠት 

👩‍🏫 ማወቅ ያለብሽ 📝

👉ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ (post pill ) ከ55% እስከ 95% ፐርሰንት እርግዝናን የመከላከል እድል አለው

👉ከልክ በላይ አካላዊ ውፍረት ያላት ሴት ላይ የመከላከል አቅሙን በተወሰነ ደረጃ ይቀንሳል

👉መደሃኒቱ በሚወሰድበት ጊዜ የእንቁላል ማኩረት ሂደት (Ovulation) ወቅትላይ ከሆንሽ እርግዝና የመከላከል እድሉን በተወሰነ መጠን ይቀንሰዋል

👉 እድሉ በጣም ትንሽ ቢሆንም መድሃኒቱን ወስደሽም እርግዝና ሊፈጠር ይችላል

👉 መደሃኒቱን ወስደሽ እርግዝና ከተፈጠረ በእርግዝናው ወይም በጽንሱ ላይ የሚያመጣው ጉዳት የለም

👉 መድሃኒቱ የአባላዘር በሽታውችን ኤች አይ ቪን ጨምሮ አይከላከልም 

👩‍⚕️ ሃኪም ማማከር ያለብሽ መቸ ነው?

👉 ከተለመደው የወር አበባሽ ውጭ ደም መፍሰስ ወይም መንጠባጠብ (spotting) ከሳምንት በላ ከቆየ

👉 ከ 3 እክሰ 5 ሳምንት የቆየ ከባድ የሆነ ከእምብርት በታች ቁርጠት ካለሽ



ስለ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ( Postpill ) ማወቅ ያለብሽ ስለ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ( Postpill ) ማወቅ ያለብሽ Reviewed by Ayduwan on February 24, 2023 Rating: 5

1 comment:

Powered by Blogger.