በክንድ ቆዳ ስር የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ (Implantable rod)

 በክንድ ቆዳ ስር የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ (Implantable rod) 

ኢምፕላንት በሴቶች በላይኛው የክንድ ቆዳ ስር የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ ሲሆን፡ እርግዝናን ለረጅም ጊዜ ለመከላከል ከሚያገለግሉ የእርግዝና መከላክያ መንገዶች ይመደባል፡፡ ማስወጣት ስታስቢ በማንኛውም ሰዓት ማስወጣት ትችያለሽ፡፡

💡 ማወቅ ያለብሽ

⭐ ኢምፕላንት እርግዝናን እንዳይፈጠር የሚከላከል #ሆርሞን የያዘ ሲሆን ይህ ሆርሞን በዝግታና ቀጣይነት ባለው መልኩ ወደ ደም ስር በመቀላቀል እርግዝናን ይከላከላል 

⭐ እርግዝናን ከ 3 እስከ 5 ዓመት ይከላከላል

⭐ እርግዝናን የመከላከል አቅሙ ከ99% በላይ ነው

⭐ በዓመት ውስጥ ከ 100 ሴት 1 ሴት መከላከያውን እየተጠቀመች ልታረግዝ ትችላለች

⭐ ለምታጠባ እናት ከወለደች ከ6 ሳምንት ጀምሮ የእርግዝና መከላከያውን መጠቀም ይቻላል 

⭐ ከዚህ በፊት የወር አበባ በብዛት መፍሰስ ወይም የወር አበባ በሚመጣበት ጊዜ ህመም ካለሽ ኢምፕላንት መጠቀም ስትጀምሪ ሊቀንሰው ይችላል

⭐ የአባላዘር በሽታን ኤች አይ ቪን ጨምሮ አይከላከልም

📌 አጠቃቀሙ

በህክምና ባለሙያ በመታገዝ በማንኛውም ሰዓት ኢምፕላንትን ክንድሽ ላይ ማስቀበር ይቻላል፡ ነገር ግን ፔሬድ በመጣ የመጀመሪያ 5 ቀናቶች ካስቀበርሽው ምንም አይነት ተጨማሪ መከላከያ አያስፈልግሽም፡ ከነዚህ ቀናቶች ውጭ ከሆነና ግንኙነት ካለሽ፡ ኢምፕላንቱን ከማስገባትሽ ከ 7 ቀን በፊት ኮንዶም ወይም ሌላ መከላከያ መጠቀም ይኖርብሻል፡፡ 

📌 የጎንዮሽ ጉዳቶቹ

👉 ለተወሰኑ ወራቶች የሚቆይ እንደ እራስ ምታት፡ ማቅለሽለሽ: የስሜት መለዋወጥ (mood swings) እና የጡት ህመም ( breast tenderness) ሊያጋጥም ይችላል

👉 የወር አበባ ጊዜን ማዛባት (የወር አበባ የሚፈስሽ መጠኑ ማነስ፡ መብዛት ወይም ረዘም ላለ ጊዜ መፍሰስ)

👉 ኢምፕላንቱን መጠቀም ስትጀምሪ የወር አበባሽ ሙሉ ለሙሉ ሊቀር ይችላል ነገር ግን መጠቀም ስታቆሚ ተመልሶ ይስተካከላል

👉 ክብደት መጨመር

👉 በጣም ያልተለመደ ነገር ግን አንዳንዴ የሚያጋጥም: ኢምፕላንቱን ለማውጣት ማስቸገር

👩‍⚕️ ሃኪም ማማከር ያለብሽ መች ነው?

👉 ኢምፕላንቱ ያለበት ቦት ላይ ስትነካኪው ከቦታው ከሌለ

👉 ኢምፕላንቱ ያለበትን ቦታ ስትነኪው መጀመሪያ ከነበርው ቅርጹን ከቀየረ

👉 ኢምፕላንቱ ያለበት ቦታ ላይ ቆዳሽ ቀለሙን ከቀየር ወይም ህመም ካለሽ

👩‍⚕️ ኢምፕላንትን መጠቀም የማይመከረው መች ነው? 

👉 ኢምፕላንቱን እርግዝና የመከላከል አቅም የሚቀንሱ መድሃኒቶች የምትወስጅ ከሆነ እንደ የኤች አይ ቪ፡ የሚጥል በሽታ፡ የሳምባ በሽታ መድሃኒቶች

👉 ምክንያቱ ያልታወቅ ከማህጸን ደመ የሚፈስሽ ከሆነ (Abnormal uterine bleeding) ወይም ከግንኙነት በኋላ መድማት ካለሽ

👉 የሚታወቅ የልብ ህመም፤ የጉበት በሽታ ካለሽ

👉 የጡት ካንሰር ካለሽ ወይም ከዚህ በፊት ከነበረሽ

በክንድ ቆዳ ስር የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ (Implantable rod) በክንድ ቆዳ ስር የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ (Implantable rod) Reviewed by Ayduwan on February 24, 2023 Rating: 5

No comments:

Powered by Blogger.