Results for February 24

ራስ ማዞር ህመም

February 24, 2023

ራስ ማዞር ምንድነው? 

አዞረኝ በምንልበት ጊዜ ከብዙ ምልክቶች እና ስሜቶች ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ራስን መሳት፣ የድካም ስሜት፣ ሚዛን ለመጠበቅ መቸገር እና ሌሎችንም ያጠቃልላል፡፡ አካባቢዎ ወይም እርሶ እየዞሩ ወይም እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ የሚሰማ አይነት ራስ ማዞር በሳንሳዊ አጠራሩ ቨርታይጎ ይባላል፡፡

በምን ምክንያት ይመጣል? 

ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ፤ እንደ የውስጠኛው የጆሮ ክፍል ችግር፣ በመኪና ሲጓዙ መታመም እና የመድሐኒቶች የጎንዮሽ ችግር ይጠቀሳሉ፡፡ አንዳንዴም ተጓዳን የጤና እክሎች እንደ ኢንፌክሺን፣ አደጋ፣ የልብ ችግር፣ የደም ዝውውር ችግር ጋር ሊያያዝ ይቻላል፡፡ በሌላ መልኩም ከማይግሪን፣ የነርቭ በሽታዎች፣ የደም ውስጥ ስኳር መጠን መቀነስ፣ ደም ማነስ፣ አንዳንድ መድሐኒቶች፣ ጭንቀት እና ውሃ አለመጠጣትም ምክንቶች ሊሆኑ ይችላለሉ፡፡

ምልክቶች

ራስ ማዞር በተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንደ መራመድ፣ ድንገት መቆም ወይም ከራስ ቅል እንቅስቃሴ ጋር ሊባባስ ይችላል፡፡ 

ብዙዎች ላይ የሚታዩ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፤

·        በዙሪያ ያሉ ነገሮች የሚንቀሳቀሱ የሚመስል ስሜት

·        ራስን መሳት 

·        ሚዛን ለመጠበቅ መቸገር

·        ጭንቅላት ላይ የሚከብድ ስሜት

ተጋላጭነት

-         በእድሜ የገፉ ሰዎች

-         ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ችግር ከነበረ

ሃኪሞት ጋር መቼ መሄድ አለቦት?

·        ተደጋጋሚ፣ ድንገት የመጣ፣ በጣም ከባድ ወይም ረዘም ላለ ጊዜ የማዞር ስሜት ከተሰማዎት

·        ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስሜቶች ካሎት

-         ሀይለኛ ራስ ምታት

-         ደረት ላይ የህመም ስሜት

-         ለመተንፈስ መቸገር

-         ለመተንፈስ መቸገር

-         እጅ እና እግር ላይ መደንዘዝ እና አለመታዘዝ

-         ራን መሳት

-         የአይን ብዥታ

-         የልብ ምት መዛባት

-         የልብ ምት መዛባት

-         ለመራመድ መቸገር

-         ማስመለስ

-         ማንቀጥቀጥ

-         የመስማት አቅም መቀነስ

ምን ማድረግ ይቻላል?

·        ሚዛኖትን በማንኛውም ጊዜ ሊስቱ እንደሚችሉ ከግምት ውስጥ ያስፈቡ

·        በድንገት ከመቀመጫ መነሳትም ሆነ መራመድን ያስወግዱ፤ ካልሆነም ከዘራ ይጠቀሙ

·        የማዞር ስሜት ከተሰማዎት ቁጭ ይበሉ ወይም ይረፉ

·        የማዞር ስሜት ከተሰማዎት ቁጭ ይበሉ ወይም ይረፉ

·        የማዞር ስሜት ካት መኪና አይንዱ ከባድ ማሽኖችን አያንቀሳቅሱ

·        ቡና፣ አልኮል፣ ጨው እና ሲጃራ አይጠቀሙ

·        በቂ ፈሳሽ ይውሰዱ

·        ጤናማ አመጋገብ ይኑሮት

·        በቂ እንቅልፍ ያግኙ

·        በቂ እንቅልፍ ያግኙ

·        ከሚያስጨንቆት ነገር ይራቁ

መልካም ጤንነት ተመኘዎሎ

ራስ ማዞር ህመም ራስ ማዞር ህመም Reviewed by Ayduwan on February 24, 2023 Rating: 5

የጡት ህመም (Breast Pain)

February 24, 2023

 የጡት ህመም | Breast Pain

የጡት ህመም የሚያስከትሉ 09 ምክንያቶች

1. ሆርሞኖች

የወር አበባ ከመጀመሩ ከሶስት እስከ አምስት ቀናት ቀደም ብሎ ህመም ይሰማዎታል፧ ከጀመሩ በኋላ ያቆማል።

ይህ የሆነበት ምክንያት የወር አበባዎ ከመጀመሩ በፊት የኢስትሮጅንና ፕሮጄስትሮን መጨመር ነው።

ነፍሰ ጡር ከሆናችሁ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ የሆርሞን ምርት እየጨመረ በመምጣቱ ጡቶዎን ይታመማሉ።

ህመሙን ለመቀነስ መውሰድ ያለቦት እርምጃዎች፦

             - ካፌይን ያስወግዱ

             - የጨው መጠን ይቀንሱ

             - ስጋራ ማጨስን መተው

             - የህመም ማስታገሻ ይውሰዱ

             - የወሊድ መከላከያ ክኒኖችን ወይም 

                የሆርሞን ምትክ ሕክምናን መቀየር 

                ሊረዳህ እንደሚችል ሐኪሞን ይጠየቁ።

2. የጡት ጉዳት

ይህ በአደጋ ምክንያት, ስፖርት በሚጫወቱበት ጊዜ ወይም በጡት ቀዶ ጥገና ምክንያት ሊከሰት ይችላል።

ህመሙ ካልተሻሻለ ወይም ከእነዚህ ምልክቶች አንዱን ካዩ ሐኪምዎን ይምክሩ፦

         - ከባድ እብጠት

         - በጡት ውስጥ እብጠት ካለ

         - መቅላት እና ሙቀት

         - የማይጠፋ ቁስል ካለ

3. በማይደገፍ ብራ ምክንያት

ተገቢው ድጋፍ ከሌለ ጡቶችን ከደረት ግድግዳ ጋር የሚያገናኙት ጅማቶች ከመጠን በላይ ይወጠሩ እና ህመም ሊያስከትሉ ይችላሉ። ሰለዚ ብራዎ ትክክለኛ ሳይዝ መሆኑን ያረጋግጡ።

4. የጡት ህመም ከደረት ግድግዳዎ የመጣ ሊሆን ይችላል

5. ጡት ማጥባት

ጡት ማጥባት አንዳንድ ጊዜ የጡት ህመም ምንጭ ሊሆን ይችላል። 

- በመነካከስ ወይም በደረቁ፣ በተሰነጠቀ ቆዳ ወይም በበሽታ ምክንያት የጡት ጫፍ ህመም ይፈጠራል  

- ተገቢ ባልሆነ መልኩ ጡት ማስያዝ በጡት ማጥባት ግዜ የጡት ህመም የሚያስከትሉ ናቸው።

6. የጡት ኢንፌክሽን

ጡት የሚያጠቡ ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ በጡት ኢንፌክሽን ይያዛሉ። የጡት ኢንፌክሽን ካለብዎ ትኩሳት ሊኖርብዎት ይችላል። በተጨማሪም የጡት መቅላት ፤ እብጠትና ህመም ይኖራል። የጡት ኢንፌክሽን ካለቦት ዶክተር ማማከር በጣም አስፈላጊ ነው

7. የጡት ህመም የመድሃኒት የጎንዮሽ ጉዳት ሊሆን ይችላል።

8. የጡት እጢ/ሲይስት ሲይስትን ለመመርመር ሐኪምዎ ማሞግራም/ አልትራሳውንድ ሊያዝሎዎ ይችላል።

9. የጡት ህመም አንዳንድ ጊዜ የጡት ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል።

በጡት ላይ ያለው ቆዳም ሊወፍር ወይም ወደ ውስጥ ሰርጎድ ሊል ይችላል። ስለ የጡት ካንሰር ካሳሰበዎት ወዲያውኑ ዶክተርዎን ያነጋግሩ።

የጡት ህመም (Breast Pain) የጡት ህመም (Breast Pain) Reviewed by Ayduwan on February 24, 2023 Rating: 5

ስለ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ( Postpill ) ማወቅ ያለብሽ

February 24, 2023

 ስለ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ( Postpill ) ማወቅ ያለብሽ 


ደንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንደ ማንኛውም የእርግዝና መከላከያ፡ ያልታቀደ እርግዝናን ለመከላከል ይረዳል፡ ከመደብኛው የእርግዝና መከላከያ ለየት የሚያደርገው፡ ግንኙንት ካደረግሽ በኋላ መወሰዱ ነው፡፡ 

ከስሙ እንደሚያመላክተው ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ለድንገተኛ ጊዜ የምንጠቀመው የእርግዝና መከላክያ ሲሆን፡ መደበኛውን የእርግዝና መከላከያ አይተካም፡፡ መደበኛውን የእርግዝና መከላከያን መጠቀም የተሻለ እርግዝናን የመከላከልና ያነሰ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንዲኖር ይረዳል፡፡

❓ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ መቸ መጠቀም ይኖርብናል?

በአስገድዶ መደፈር ጊዜ፡ ኮንዶም ሲቀደድ ወይም በግንኙነት ጊዜ ሲወጣ፡ መደበኛ የእርግዝና መከላከያ ፒልስ አንድ ሁለት ቀን መውሰድ ከረሳሽ

🕒 አወሳሰዱ

ግንኙነት ባደረግሽ እስከ 72 ሰዓት በሉት ጊዜያቶች መውሰድ ትችያለሽ፡ ነገር ገን በ 12 ሰዓት ውስጥ ቶሎ መውሰድ መድሃኒቱ እርግዝናን የመከላከል እድሉን እንዲጨመር ያደርገዋል፡፡ 

⚠ መድሃኒቱን በምትወስጅበት ጊዜ የሚከሰቱ የጎንዮሽ ጉዳቶች

👉 ማቅለሽለሽ፡ ማስታውክ፡ ድካም፡ እራስ ምታት፡ የጡት መወጠር ህመም  

👉 የወር አበባ መዛባት፡ ከመደበኛው ቀን ቶሎ ወይም ዘግይቶ መምጣት፡ ብዛት ያለው ወይም ያነሰ የወር አበባ እንዲፈስሽ ያደርጋል፡

👉 መድሃኒቱ ከተወሰደ በኋላ ለአንድ ለሁለት ቀን የሚቆይ መጠኑ ትንሽ ደም መፍሰስ (spotting) 

👉 ከእምብርት በታች ቁርጠት 

👩‍🏫 ማወቅ ያለብሽ 📝

👉ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ (post pill ) ከ55% እስከ 95% ፐርሰንት እርግዝናን የመከላከል እድል አለው

👉ከልክ በላይ አካላዊ ውፍረት ያላት ሴት ላይ የመከላከል አቅሙን በተወሰነ ደረጃ ይቀንሳል

👉መደሃኒቱ በሚወሰድበት ጊዜ የእንቁላል ማኩረት ሂደት (Ovulation) ወቅትላይ ከሆንሽ እርግዝና የመከላከል እድሉን በተወሰነ መጠን ይቀንሰዋል

👉 እድሉ በጣም ትንሽ ቢሆንም መድሃኒቱን ወስደሽም እርግዝና ሊፈጠር ይችላል

👉 መደሃኒቱን ወስደሽ እርግዝና ከተፈጠረ በእርግዝናው ወይም በጽንሱ ላይ የሚያመጣው ጉዳት የለም

👉 መድሃኒቱ የአባላዘር በሽታውችን ኤች አይ ቪን ጨምሮ አይከላከልም 

👩‍⚕️ ሃኪም ማማከር ያለብሽ መቸ ነው?

👉 ከተለመደው የወር አበባሽ ውጭ ደም መፍሰስ ወይም መንጠባጠብ (spotting) ከሳምንት በላ ከቆየ

👉 ከ 3 እክሰ 5 ሳምንት የቆየ ከባድ የሆነ ከእምብርት በታች ቁርጠት ካለሽ



ስለ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ( Postpill ) ማወቅ ያለብሽ ስለ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ( Postpill ) ማወቅ ያለብሽ Reviewed by Ayduwan on February 24, 2023 Rating: 5

እርግዝና መከላከያ መንገዶች (Birth control methods )

February 24, 2023

 እርግዝና መከላከያ መንገዶች (Birth control methods )



አንድ ሴት እርግዝናን መከላከል ስታስብ ከብዙ አይነት የእርግዝና መከላከያ አማራጮች ወስጥ አንዱን መርጣ መጠቀም ትችላለች፡፡ የምትጠቀሚወን የእርግዝና መከላከያ በተለያዩ ምክያቶች ላንች ተስማሚ የሆነውን መርጠሽ መጠቀም ትችያለሽ ( ለመሳሌ ከጤናሽ አንጻር፡ ልጅ ለመውለድ ያሰብሽበት ጊዜን በማገናዘብ) 

❓ የትኛው የተሻል የእርግዝና መከላከያ ነው? 

ለሁሉም ሴት የሚሆንና ይሄ የተሻለ ነው ብሎ ማስቀመጥ አይቻልም ነገር ግን ሃኪምሽ ጋር በመማከር ላንች ፍላጎት ወይም እቅድ ተስማሚ የሆነ የእርግዝና መከላከያ መርጠሽ መጠቀም ትችያለሽ፡፡

👩‍⚕️ የእርግዝና ምከላከያ ከመውሰድሽ በፊት ከሃኪምሽ ጋር መመካከር ያለብሽ

📌 መቸ ማርገዝ እንዳሰብሽ

📌 እያንዳንዱ የእርግዝና መከላከያ ምን ያክል የመከላከል አቅም እንዳለው

📌 ያሉት የጎንዮሽ ጉዳቶቹ

📌 በምን ያክል ጊዜ ግንኙነት እንደምታደርጊ

📌 ምን ያክል የወንድ ጓደኛ እንዳለሽ

📌 አሁን ያለሽ የጤና ሁኔታ

🙋🏽‍♀️ ማወቅ ያለብሽ 

የእርግዝና መከላከያ እየተጠቀምሽ በተወሰነ ደረጃ ቢሆንም እርግዝና የመፈጠር እድል ይኖረዋል፡ ነገር ግን በአግባቡ ከተጠቀምሽ እርግዝና የመፈጠር እድሉ በጣም አነስተኛ ነው፡፡

🤰 እርግዝና የመከላከያ መንገዶች

👉 የሴቷን ወይም የወንዱን የዘር ፍሬ በቋሚነት በህክምና ማቋረጥ (sterilization)

👉 ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ነገር ግን በማንኛውም ጊዜ ማስወጣት የሚቻል የእርግዝና መከላከያ

 (ማህጸን ወስጥ የሚቀመጥ ሉፕ፡ በክንድ ላይ የሚቀበር ኢምፕላንት፣ ከ3 እስክ 10 ዓመት የሚቆይ)

👉 ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ሆርሞናል የእርግዝና መከላከያ (በየቀኑ የሚወሰድ ፒልስ፡ በየ 3 ወር የሚወሰድ መርፌ)

👉 የወንዱን ዘር ፍሬ ከሴቷ እንቁላ ጋር እንዳይገናኝ መከላከያ መንገድ (ኮንዶም)

👉 ተፈጥሯዊ የወር አበባ ኡደትሽን በመቁጠረ፡ የእንቁላል ማኩረት ጊዜን (ovulation time) እየቆጠሩ ግንኙነት ባለ ማድረግ


እርግዝና መከላከያ መንገዶች (Birth control methods ) እርግዝና መከላከያ መንገዶች (Birth control methods ) Reviewed by Ayduwan on February 24, 2023 Rating: 5

ኮፐር ሉፕ (𝐂𝐨𝐩𝐩𝐞𝐫 𝐢𝐧𝐭𝐫𝐚𝐮𝐭𝐞𝐫𝐢𝐧𝐞 𝐝𝐞𝐯𝐢𝐜𝐞) 𝐈𝐔𝐃

February 24, 2023

 ኮፐር ሉፕ (𝐂𝐨𝐩𝐩𝐞𝐫 𝐢𝐧𝐭𝐫𝐚𝐮𝐭𝐞𝐫𝐢𝐧𝐞 𝐝𝐞𝐯𝐢𝐜𝐞) 𝐈𝐔𝐃 

ለረጅም ጊዜ ከሚያገለግሉ የእርግዝና መከላክያ ምንገዶች የሚመደብ ሲሆን፡ ማስወጣት ስታስቢ በማንኛውም ሰዓት ማስወጣት ትችያለሽ፡፡

💡 ማወቅ ያለብሽ

⭐ ምንም አይነት የሆርሞን ቅመም የለውም ሰለዚህ በሆርሞን ምክኒያት የሚመጣ የጎንዮሽ ጉዳት የለውም

⭐ እርግዝናን ለ10 ዓመት ይከላከላል

⭐ እርግዝና የመከላከል አቅሙ ከ99% በላይ ነው 

⭐ በዓመት ውስጥ ከ 100 ሴት 1 ሴት መከላከያውን እየተጠቀመች ልታረግዝ ትችላለች

⭐ የምታጠባ እናት የእርግዝና መከላከያውን መጠቀም ትችላለች

⭐ የአባላዘር በሽታን ኤች አይ ቪን ጨምሮ አይከላከልም

⭐ ሉፕ ከመጠቀምሽ በፊት የቆየ ኢንፌክሽንና የአባላዘር በሽታውች ካለሽ መጀመሪያ መታከም ይኖርብሻል

⭐ ሉፕ ካስገባሽ በኋላ የመጀመሪያ 3 እስክ 6 ሳምንት ባሉት ጊዜያት ህክምና ቦታ ሄደሽ ማታየት ይኖርብሻል

📌 አጠቃቀሙ

በህክምና ባላሙያ በመታገዝ በማንኛውም ሰዓት ሉፕን ወደ ማህጸን በማስገባት መጠቀም ይቻላል፡ ነገር ግን ፔሬድ በመጣ የመጀመሪያ 5 ቀናቶች ካስገባሽው ምንም አይነት ተጨማሪ መከላከያ አያስፈልግሽም፡ ከነዚህ ቀናቶች ውጭ ከሆነና ግንኙነት ካለሽ፡ ሉፕ ከማስገባትሽ ከ 7 ቀን በፊት ኮንዶም ወይም ሌላ መከላከያ መጠቀም ይኖርብሻል፡፡ 

📌 ሉፕ ቦታው ላይ መኖሩን እንዴት ማውቅ ይቻላል?

ከሉፑ የታችኛው ጫፍ ላይ የታሰሩ ሁለት ክሮች ይኖራሉ፡ ሉፕ ያስገባልሽ የህክምና ባለሞያ እንዴት ሉፕ ቦታው ላይ መኖሩን ማወቅ እንደምትች ይነገርሻል፡፡ አልፎ አልፎ ሉፑ በቦታው ላይ መኖሩን መፈተሽ ይኖርብሻል፡፡

📌 የጎንዮሽ ጉዳቶች

👉 የወር አበባ መቅረት 

👉 በወር አበባ መሃል ደም መፍሰስ

👉 ለተወሰኑ ወራቶች የወር አበባ መብዛትና ረዘም ላለ ጊዜ መፍሰስ ሊያጋጥም ይችላል

👉 እድሉ በጣም ትንሽ ቢሆንም ሉፕ ከስገባሽ በኋላ ሊወጣ ይችላል

👉 እድሉ በጣም ትንሽ ቢሆንም ሉፕ ካስገባሽ በኋል ኢንፌክሽን ሊፈጠር ይችላል 

👉 ሉፕ እየተጠቀምሽ እርግዝና ከተፈጠረ ከማህጸን ውጭ እርግዝና የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው

📌 በጣም ያልተለመደ ነገር ግን አደኛ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት

👉 𝐏𝐞𝐥𝐯𝐢𝐜 𝐢𝐧𝐟𝐥𝐚𝐦𝐦𝐚𝐭𝐨𝐫𝐲 𝐝𝐢𝐬𝐞𝐚𝐬𝐞

👉 ሉፕ ቦታውን መልቀቅ 

👉 በማህጸን ግድግዳ ማለፍ 

📌 ሉፕ ካስገባሽ በኋላ ለመጀመሪ ወራቶች ኢንፌክሽን ፈጥሮ እንዳይሆን የጥንቃቂ ምልክቶች

ትኩሳት፤ ከእምብርት በታች ህመምና ሽታ ያለው ያልተለመደ ፈሳሽ ካለሽ የኢንፌክሽን ምልክቶች ስለሚሆኑ ሃኪም ማማከር ይኖርብሻል፡፡

👩‍⚕️ ሉፕን መጠቀም የማይመከረው መቸነው? 

👉 ህክምና ያልተደረገለት የአባላዘር በርሽታ ካለሽ

👉 የ 𝐩𝐞𝐥𝐯𝐢𝐜 ኢንፊክሽን ከዚህ በፊት ከነበረሽ

👉 ምክንያቱ ያልታወቅ ከማህጸን ደመ የሚፈስሽ ከሆነ (𝐀𝐛𝐧𝐨𝐫𝐦𝐚𝐥 𝐮𝐭𝐞𝐫𝐢𝐧𝐞 𝐛𝐥𝐞𝐞𝐝𝐢𝐧𝐠 ) ወይም ከግንኙነት በኋላ መድማት ካለሽ

👉 ከዚህ በፊት ከማህጸን ውጭ እርግዝና አጋጥሞሽ ከነበር


ኮፐር ሉፕ (𝐂𝐨𝐩𝐩𝐞𝐫 𝐢𝐧𝐭𝐫𝐚𝐮𝐭𝐞𝐫𝐢𝐧𝐞 𝐝𝐞𝐯𝐢𝐜𝐞) 𝐈𝐔𝐃 ኮፐር ሉፕ (𝐂𝐨𝐩𝐩𝐞𝐫 𝐢𝐧𝐭𝐫𝐚𝐮𝐭𝐞𝐫𝐢𝐧𝐞 𝐝𝐞𝐯𝐢𝐜𝐞) 𝐈𝐔𝐃 Reviewed by Ayduwan on February 24, 2023 Rating: 5

ሆርሞናል መርፌ የእርግዝ መከላከያ (Contraceptive Injection)

February 24, 2023

  



ሆርሞናል መርፌ የእርግዝና መከላከያ፡ ከመደበኛ የእርግዝና መከላከያ የሚመደብ ሲሆን፡ እርግዝናን ለ 3 ወራቶች ይከላከላል፡፡



 💡 ማወቅ ያለብሽ

 ⭐ (Perfect use) በየ 3 ወሩ በሰዓቱና በአግባቡ መርፌው ከተወሰደ 99% እርግዝናን ይከላከላል፡ በዓመት ውስጥ ከ 100 ሴት 1 ሴት መከላከያውን በትክክል እየተጠቀመች ልታረግዝ ትችላለች

 ⭐ (Typical use) በመደበኛ አጠቃቀም፡ 94% እርግዝናን ይከለከላል፡ በዓመት ውስጥ ከ 100 ሴት 6 ሴት መከላከያውን እየተጠቀመች ልታረግዝ ትችላለች 

 ⭐ ለሌላ ህክምና የምትወስጃቸው መድሃኒቶች፡ መርፌውን እርግዝና የመከላከል አቅሙን #አይቀንሰውም 

 ⭐ ቅመምነቱ ከሰውነትሽ እስኪወጣ፡ እርግዝናን እስከ አንድ አመት ያክል ሊከለክልሽ ይችላል፡ በቅርብ የመውለድ እቅድ ካለሽ መርፌው አይመከርም

 ⭐ ለምታጠባ እናት ከወለደች ከ6 ሳምንት ጀምሮ የእርግዝና መከላከያውን መጠቀም ይቻላል 

 ⭐ አንዳንድ ሴት ላይ፡ ከዚህ በፊት የወር አበባ በብዛት መፍሰስ ወይም የወር አበባ በሚመጣበት ጊዜ ህመም ካለሽ መርፌውን መጠቀም ስትጀምሪ ሊቀንሰው ይችላል

 ⭐ የአባላዘር በሽታን፡ ኤች አይ ቪን ጨምሮ አይከላከልም

 📌 አወሳሰዱ በህክምና ባለሙያ በመታገዝ በማንኛውም ሰዓት መርፌውን መወጋት ይቻላል፡ ነገር ግን ፔሬድ በመጣ የመጀመሪያ 5 ቀናቶች ከተወጋሽ፡ ምንም አይነት ተጨማሪ መከላከያ አያስፈልግሽም፡ ከነዚህ ቀናቶች ውጭ ከሆነና ግንኙነት ካለሽ፡ መርፌውን ከመውሰድሽ ከ 7 ቀን በፊት ኮንዶም ወይም ሌላ መከላከያ መጠቀም ይኖርብሻል፡፡ 

 📌 የጎንዮሽ ጉዳቶች 

 👉 መርፌውን እየተጠቀምሽና ካቆምሽ በኋላ ለተወሰኑ ወራቶች የሚቆይ የወር አበባ መዛባት (በመሃል ደም መፍሰስ፡ በብዛት መፍሰስ፡ ለአጭር ጊዜ መፍሰስ፡ ፔሬድ ሳይመጣ ወሩን ማሳለፍ፡ ወይም ጭራሽ ለተወሰነ ጊዜ የወር አበባ መቅረት) 

 👉 እራስ ምታት 

 👉 ክብደት መጨመር 

 👉 የስሜት ወይም የባህሪ ለውጥ (mood swings)

 👉 የጡት ህመም (breast tenderness) 

 👉 የራስ ጸጉር መነቃቀል/መሳሳት (hair loss)

 👉 የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ 

 👉 ለረጅም ጊዜ ከተወሰደ የአጥንት መሳሳት ያስከትላል

 📌 መርፌውን መጠቀም የማይመከረው መች ነው?

 👉 መከላከያውን እንዳቆምሽ ቶሎ ወይም በ አንድ ዓመት ውስጥ ማርገዝ ካሰብሽ 

 👉 ምክንያቱ ያልታወቅ፡ በወር አበባ መሃል ደመ የሚፈስሽ ከሆነ ወይም ከግንኙነት በኋላ መድማት ካለሽ 

 👉 የሚታወቅ የስኳር በሽታ ካለሽ 

 👉 የሚታወቅ የልብ ህመም፤ የጉበት በሽታ ካለሽ

 👉 የጡት ካንሰር ካለሽ ወይም ከዚህ በፊት ከነበረሽ

 👉 የሚታወቅ migraine ካለሽ

ሆርሞናል መርፌ የእርግዝ መከላከያ (Contraceptive Injection) ሆርሞናል መርፌ የእርግዝ መከላከያ (Contraceptive Injection) Reviewed by Ayduwan on February 24, 2023 Rating: 5

በክንድ ቆዳ ስር የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ (Implantable rod)

February 24, 2023

 በክንድ ቆዳ ስር የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ (Implantable rod) 

ኢምፕላንት በሴቶች በላይኛው የክንድ ቆዳ ስር የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ ሲሆን፡ እርግዝናን ለረጅም ጊዜ ለመከላከል ከሚያገለግሉ የእርግዝና መከላክያ መንገዶች ይመደባል፡፡ ማስወጣት ስታስቢ በማንኛውም ሰዓት ማስወጣት ትችያለሽ፡፡

💡 ማወቅ ያለብሽ

⭐ ኢምፕላንት እርግዝናን እንዳይፈጠር የሚከላከል #ሆርሞን የያዘ ሲሆን ይህ ሆርሞን በዝግታና ቀጣይነት ባለው መልኩ ወደ ደም ስር በመቀላቀል እርግዝናን ይከላከላል 

⭐ እርግዝናን ከ 3 እስከ 5 ዓመት ይከላከላል

⭐ እርግዝናን የመከላከል አቅሙ ከ99% በላይ ነው

⭐ በዓመት ውስጥ ከ 100 ሴት 1 ሴት መከላከያውን እየተጠቀመች ልታረግዝ ትችላለች

⭐ ለምታጠባ እናት ከወለደች ከ6 ሳምንት ጀምሮ የእርግዝና መከላከያውን መጠቀም ይቻላል 

⭐ ከዚህ በፊት የወር አበባ በብዛት መፍሰስ ወይም የወር አበባ በሚመጣበት ጊዜ ህመም ካለሽ ኢምፕላንት መጠቀም ስትጀምሪ ሊቀንሰው ይችላል

⭐ የአባላዘር በሽታን ኤች አይ ቪን ጨምሮ አይከላከልም

📌 አጠቃቀሙ

በህክምና ባለሙያ በመታገዝ በማንኛውም ሰዓት ኢምፕላንትን ክንድሽ ላይ ማስቀበር ይቻላል፡ ነገር ግን ፔሬድ በመጣ የመጀመሪያ 5 ቀናቶች ካስቀበርሽው ምንም አይነት ተጨማሪ መከላከያ አያስፈልግሽም፡ ከነዚህ ቀናቶች ውጭ ከሆነና ግንኙነት ካለሽ፡ ኢምፕላንቱን ከማስገባትሽ ከ 7 ቀን በፊት ኮንዶም ወይም ሌላ መከላከያ መጠቀም ይኖርብሻል፡፡ 

📌 የጎንዮሽ ጉዳቶቹ

👉 ለተወሰኑ ወራቶች የሚቆይ እንደ እራስ ምታት፡ ማቅለሽለሽ: የስሜት መለዋወጥ (mood swings) እና የጡት ህመም ( breast tenderness) ሊያጋጥም ይችላል

👉 የወር አበባ ጊዜን ማዛባት (የወር አበባ የሚፈስሽ መጠኑ ማነስ፡ መብዛት ወይም ረዘም ላለ ጊዜ መፍሰስ)

👉 ኢምፕላንቱን መጠቀም ስትጀምሪ የወር አበባሽ ሙሉ ለሙሉ ሊቀር ይችላል ነገር ግን መጠቀም ስታቆሚ ተመልሶ ይስተካከላል

👉 ክብደት መጨመር

👉 በጣም ያልተለመደ ነገር ግን አንዳንዴ የሚያጋጥም: ኢምፕላንቱን ለማውጣት ማስቸገር

👩‍⚕️ ሃኪም ማማከር ያለብሽ መች ነው?

👉 ኢምፕላንቱ ያለበት ቦት ላይ ስትነካኪው ከቦታው ከሌለ

👉 ኢምፕላንቱ ያለበትን ቦታ ስትነኪው መጀመሪያ ከነበርው ቅርጹን ከቀየረ

👉 ኢምፕላንቱ ያለበት ቦታ ላይ ቆዳሽ ቀለሙን ከቀየር ወይም ህመም ካለሽ

👩‍⚕️ ኢምፕላንትን መጠቀም የማይመከረው መች ነው? 

👉 ኢምፕላንቱን እርግዝና የመከላከል አቅም የሚቀንሱ መድሃኒቶች የምትወስጅ ከሆነ እንደ የኤች አይ ቪ፡ የሚጥል በሽታ፡ የሳምባ በሽታ መድሃኒቶች

👉 ምክንያቱ ያልታወቅ ከማህጸን ደመ የሚፈስሽ ከሆነ (Abnormal uterine bleeding) ወይም ከግንኙነት በኋላ መድማት ካለሽ

👉 የሚታወቅ የልብ ህመም፤ የጉበት በሽታ ካለሽ

👉 የጡት ካንሰር ካለሽ ወይም ከዚህ በፊት ከነበረሽ

በክንድ ቆዳ ስር የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ (Implantable rod) በክንድ ቆዳ ስር የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ (Implantable rod) Reviewed by Ayduwan on February 24, 2023 Rating: 5
Powered by Blogger.