ኮፐር ሉፕ (𝐂𝐨𝐩𝐩𝐞𝐫 𝐢𝐧𝐭𝐫𝐚𝐮𝐭𝐞𝐫𝐢𝐧𝐞 𝐝𝐞𝐯𝐢𝐜𝐞) 𝐈𝐔𝐃

 ኮፐር ሉፕ (𝐂𝐨𝐩𝐩𝐞𝐫 𝐢𝐧𝐭𝐫𝐚𝐮𝐭𝐞𝐫𝐢𝐧𝐞 𝐝𝐞𝐯𝐢𝐜𝐞) 𝐈𝐔𝐃 

ለረጅም ጊዜ ከሚያገለግሉ የእርግዝና መከላክያ ምንገዶች የሚመደብ ሲሆን፡ ማስወጣት ስታስቢ በማንኛውም ሰዓት ማስወጣት ትችያለሽ፡፡

💡 ማወቅ ያለብሽ

⭐ ምንም አይነት የሆርሞን ቅመም የለውም ሰለዚህ በሆርሞን ምክኒያት የሚመጣ የጎንዮሽ ጉዳት የለውም

⭐ እርግዝናን ለ10 ዓመት ይከላከላል

⭐ እርግዝና የመከላከል አቅሙ ከ99% በላይ ነው 

⭐ በዓመት ውስጥ ከ 100 ሴት 1 ሴት መከላከያውን እየተጠቀመች ልታረግዝ ትችላለች

⭐ የምታጠባ እናት የእርግዝና መከላከያውን መጠቀም ትችላለች

⭐ የአባላዘር በሽታን ኤች አይ ቪን ጨምሮ አይከላከልም

⭐ ሉፕ ከመጠቀምሽ በፊት የቆየ ኢንፌክሽንና የአባላዘር በሽታውች ካለሽ መጀመሪያ መታከም ይኖርብሻል

⭐ ሉፕ ካስገባሽ በኋላ የመጀመሪያ 3 እስክ 6 ሳምንት ባሉት ጊዜያት ህክምና ቦታ ሄደሽ ማታየት ይኖርብሻል

📌 አጠቃቀሙ

በህክምና ባላሙያ በመታገዝ በማንኛውም ሰዓት ሉፕን ወደ ማህጸን በማስገባት መጠቀም ይቻላል፡ ነገር ግን ፔሬድ በመጣ የመጀመሪያ 5 ቀናቶች ካስገባሽው ምንም አይነት ተጨማሪ መከላከያ አያስፈልግሽም፡ ከነዚህ ቀናቶች ውጭ ከሆነና ግንኙነት ካለሽ፡ ሉፕ ከማስገባትሽ ከ 7 ቀን በፊት ኮንዶም ወይም ሌላ መከላከያ መጠቀም ይኖርብሻል፡፡ 

📌 ሉፕ ቦታው ላይ መኖሩን እንዴት ማውቅ ይቻላል?

ከሉፑ የታችኛው ጫፍ ላይ የታሰሩ ሁለት ክሮች ይኖራሉ፡ ሉፕ ያስገባልሽ የህክምና ባለሞያ እንዴት ሉፕ ቦታው ላይ መኖሩን ማወቅ እንደምትች ይነገርሻል፡፡ አልፎ አልፎ ሉፑ በቦታው ላይ መኖሩን መፈተሽ ይኖርብሻል፡፡

📌 የጎንዮሽ ጉዳቶች

👉 የወር አበባ መቅረት 

👉 በወር አበባ መሃል ደም መፍሰስ

👉 ለተወሰኑ ወራቶች የወር አበባ መብዛትና ረዘም ላለ ጊዜ መፍሰስ ሊያጋጥም ይችላል

👉 እድሉ በጣም ትንሽ ቢሆንም ሉፕ ከስገባሽ በኋላ ሊወጣ ይችላል

👉 እድሉ በጣም ትንሽ ቢሆንም ሉፕ ካስገባሽ በኋል ኢንፌክሽን ሊፈጠር ይችላል 

👉 ሉፕ እየተጠቀምሽ እርግዝና ከተፈጠረ ከማህጸን ውጭ እርግዝና የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው

📌 በጣም ያልተለመደ ነገር ግን አደኛ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት

👉 𝐏𝐞𝐥𝐯𝐢𝐜 𝐢𝐧𝐟𝐥𝐚𝐦𝐦𝐚𝐭𝐨𝐫𝐲 𝐝𝐢𝐬𝐞𝐚𝐬𝐞

👉 ሉፕ ቦታውን መልቀቅ 

👉 በማህጸን ግድግዳ ማለፍ 

📌 ሉፕ ካስገባሽ በኋላ ለመጀመሪ ወራቶች ኢንፌክሽን ፈጥሮ እንዳይሆን የጥንቃቂ ምልክቶች

ትኩሳት፤ ከእምብርት በታች ህመምና ሽታ ያለው ያልተለመደ ፈሳሽ ካለሽ የኢንፌክሽን ምልክቶች ስለሚሆኑ ሃኪም ማማከር ይኖርብሻል፡፡

👩‍⚕️ ሉፕን መጠቀም የማይመከረው መቸነው? 

👉 ህክምና ያልተደረገለት የአባላዘር በርሽታ ካለሽ

👉 የ 𝐩𝐞𝐥𝐯𝐢𝐜 ኢንፊክሽን ከዚህ በፊት ከነበረሽ

👉 ምክንያቱ ያልታወቅ ከማህጸን ደመ የሚፈስሽ ከሆነ (𝐀𝐛𝐧𝐨𝐫𝐦𝐚𝐥 𝐮𝐭𝐞𝐫𝐢𝐧𝐞 𝐛𝐥𝐞𝐞𝐝𝐢𝐧𝐠 ) ወይም ከግንኙነት በኋላ መድማት ካለሽ

👉 ከዚህ በፊት ከማህጸን ውጭ እርግዝና አጋጥሞሽ ከነበር


ኮፐር ሉፕ (𝐂𝐨𝐩𝐩𝐞𝐫 𝐢𝐧𝐭𝐫𝐚𝐮𝐭𝐞𝐫𝐢𝐧𝐞 𝐝𝐞𝐯𝐢𝐜𝐞) 𝐈𝐔𝐃 ኮፐር ሉፕ (𝐂𝐨𝐩𝐩𝐞𝐫 𝐢𝐧𝐭𝐫𝐚𝐮𝐭𝐞𝐫𝐢𝐧𝐞 𝐝𝐞𝐯𝐢𝐜𝐞) 𝐈𝐔𝐃 Reviewed by Ayduwan on February 24, 2023 Rating: 5

No comments:

Powered by Blogger.