Iron በእርግዝና ጊዜ


> አንድ በእርግዝና ወቅት ላይ ያለች ሴት 1 ግራም Iron ለመላ የእርግዝና ጊዜዋ ያስፈልጋታል።

   - 500ሚ.ግ - ቀይ የደም ህዋሶችሽን ለመጨመር

   - 300ሚ.ግ - ወደ ህፃንሽ የሚሄድ

   - 200ሚ.ግ - በተለያየ ምክንያት ከሰውነትሽ ለምታጪው Iron የሚተካ ይሆናል

♧ ስለዚህ በእርግዝናሽ ጊዜ ከ 30-60 ሚ.ግ elemental Iron በቀን ያስፈልግሻል ማለት ነው።

♧ ብዙውን ጊዜ በእርግዝናሽ ሰዓት የሚከሰተው የደም ማነስ ከIron እጥረት የመጣ ሲሆን እሱም Iron deficiency Anemia እንለዋለን።

♧ እሱም የሚታወቀው የደም መጠንሽን የሚለካው Hgb (Hemoglobin) የተባለው ቀይ የደም ህዋስሽ ላይ የሚገኝ መጠኑ ከ 10gm% በታች ሲሆን ነው።

♧ ስለዚህ በመጀመሪያው እንዲሁም በሁለተኛው የቅድመ ወሊድ ክትትል ሂደትሽ ላይ የሚሠጡሽን ሠላሳ ሠላሳ የIron እንክብሎች (Tablets) ,አንድም ሳታስቀሪ ተጠቀሚ ።

ላንቺ የሚሰጠው ጥቅም

       - ከእርግዝና ጋር ተያይዞ ለሚመጣ የደም ማነስ ለመከላከል

       - የሰውነትሽን የIron መጠን ለመጨመር

> ለፅንሱ የሚሰጠው ጥቅም

      - የደም ማነስን ይከላከላል

      - በቂ የ ኦክስጅን አቅርቦት ይጨምራል

      - ለፅንሱ የጭንቅላት እድገት ጠቃሚ ነው

> አወሳሰድ

♧ Iron Tablets በባዶ ሆድ ቢወሰድ ወደ ደምሽ የሚገባው የIron መጠን ከፍተኛ ይሆናል ። 

♧  ነገር ግን የማቅለሽለሽ እንዲሁም ጨጓራሽን የማቃጠል ስሜት ካለሽ ምግብ ከተመገብሽ በኋላ ብትወስጅው መጠኑ ይቀንስ እንጂ ጥቅሙ እጅጉን የላቀ ነው። 

♧ ከፍተኛ የሆነ ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ ካለ እንክብሉ(Tablet) ወደ ሽሮፕ(Syrup) ሊቀየር ይችላል።

> ሳልወስድ ብተወው ካልሽ የሚከሰቱ ጉዳቶች

🩸በእርግዝና ጊዜ የደም ማነስ (ላንቺም ለፅንሱም)

🩸በቂ የIron መጠን ስላሌለሽ ከወሊድ በኋላ የደም ማነስ በተለይ በወሊድ ጊዜ ደም ከፈሰሰ

🩸 የደም ማነሱ መጠኑ በጣም ከፍተኛ ከሆነ ደግሞ የልብ ድካምን(Cardiac Failure) ሊያስከትልብሽ ይችላል።



Iron በእርግዝና ጊዜ  Iron በእርግዝና ጊዜ Reviewed by Ayduwan on February 25, 2023 Rating: 5

No comments:

Powered by Blogger.