በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት ወይም (preclampsia)

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት ወይም (preclampsia)
የእርግዝና ደም ግፊት የሚከሰተዉ መቼ ነዉ? አብዛኛዉን ግዜ በርግዝና 2ኛዉ አጋማሽ ማለትም ከሃያ ሳምንት በኋላ ይከሰታል፡፡ልጅ ከተወለደ በኋላም ሊከሰት ይችላል፡፡ መንስኤዉ ምንድን ነዉ? በተለያየ ጊዜ ጥናቶች ቢደረጉም አንዳንድ ሴቶች ለምን በእርግዝና ወቅት ደም ግፊት እንደሚይዛቸዉ በትክክል አልታወቀም ወይም የዚህን በሽታ መንስኤ ለይቶ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተጠቀሱት ምክንያቶች ተጋላጭ ያደርጋቸዋል፡፡  እርግዝና የመጀመሪያቸዉ የሆነ  ከዚህ በፊት በእርግዝና ግዜ የደም ግፊት የታየባቸዉ ወይም በቤተሰብ ዉስጥ ተመሳሳይ ታሪክ ያላቸዉ  ከዚህ በፊት የደም ግፊት ፤ የኩላሊት ወይም ሁለቱም በሽታ የነበረባቸዉ  እድሜያቸዉ ከ 40 አመት በላይ የሆኑ  እርግዝናዉ መንታ ወይም ከዚያ በላይ ሲሆን  እንደ ስኳር አይነት ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸዉ  ከመጠን በላይ የሰዉነት ክብደት አንዲት ነፍሰጡር ደም ግፊት ቢኖርባት በልጇ ላይ ምን ሊያስከትል ይችላል?  የልጁ ክብደት ከእርግዝና ጊዜ ጋር ሲታይ የቀነሰ ይሆናል  የዉሃ ሽንት መቀነስ  በእትብት በኩል ለልጁ የሚደርሰዉ ደም መቀነስ  እንዲሁም ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እንዳለ ሊሞት ይችላል ምልክቶቹ ምንድን ናቸዉ?  የበሽታዉ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ምንም አይነት ምልክት አይታይም፡፡ በምርመራ ጊዜ የግፊት መጨመር (≥140/90) እና ሽንት ዉስጥ ያለዉ ፕሮቲን መጨመር ይታያል፡፡ ህመሙ አደገኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ  ከባድ ራስ ምታት  የእይታ ለዉጥ(የእይታ ብዥ ማለት፤ የእይታ መጋረድ)  ትንፋሽ ማጠር  በሆድ የላይኛዉ ክፍል ላይ ከባድ የሆነ የህመም ስሜት  ከፍተኛ የደም ግፊት(≥160/110)  የፊት እና የእጆች ማበጥ በእርግዝና ወቅት የሚከሰትየደም ግፊትን ለመከላከል ምን ይደረግ? 1. ሁሉም ነፍሰጡር የቅድመ ወሊድ ክትትል እንዲያደርጉ ማበረታታት ፡- የደም ግፊቱ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ትንፋሽ ሲያጥራቸዉ፤ ሲያንቀጠቅጣቸዉ እና አእምሮአቸዉን ሲያስታቸዉ ወደ ህክምና የሚሄዱ ነፍሰጡሮች በተደጋጋሚ ያጋጥማሉ፡፡ይህ ከመከሰቱ በፊት እርዳታ ማግኘት እንድትችል የቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡ 2. ደም ግፊት ያለባት ለመጸነስ የምታስብ ሴት የጤና ባለሙያ በማማከር ህመሙ በጤናዋ ላይ ችግር አለመፍጠሩን ለማጣራት የቅድመ እርግዝና ምርመራ ማድረግ ይኖርባታል፡፡ 3. ክብደቷ ከተገቢዉ በላይ ከሆነ ከእርግዝና በፊት መቀነስ ይኖርባታል፡፡ 4. የስኳር ህመም ያለባት ሴት ከማርገዟ በፊት ህመሟን በቁጥጥር ስር ማድረግ አለባት፡፡ 5. የእርግዝና ደም ግፊት የተጋለጡ እናቶችን ለመለየና የመከሰት እድሉን ለመቀነስ የቅድመ ወሊድ ክትትል በመጀመሪያ ሶስት ወር መጀመር
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት ወይም (preclampsia) በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት ወይም (preclampsia) Reviewed by Ayduwan on April 05, 2023 Rating: 5

No comments:

Powered by Blogger.