♡ የስኳር ህመም ምንድን ነው?

  


♡ የስኳር ህመም ምንድን ነው?

የስኳር ህመም በደማችን ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከተገቢው በላይ መጨመር ሲሆን የሚከሰተውም ቆሽት የተባለው የሰውነት ክፍል ኢንሱሊን /Insulin/ የተባለውን ሆርሞን በበቂ ወይም ጭራሹን ማመንጨት ሲያቅተው ወይም የተመረተውን ኢንሱሊን በአግባቡ መጠቀም መስራት ሲያቅተው ነው፡፡

የስኳር ህመም ማንን ይይዛል?

• የስኳር ህመም እድሜ፣ ብሄር፣ ፆታ፣ የኑሮ ደረጃ ሳይል በሁሉም ሰው ሊከሰት የሚችል ህመም ነው፡፡

♡ ለስኳር ህመም ይበልጥ ተጋላጭ ማን ነው?

• የዕድሜ መጨመር /መግፋት

• ከመጠን ያለፈ ውፍረት /

• በቅርብ ቤተሰብ የስኳር ህመም መኖር

• ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ

• ከዚህ ቀደም በእርግዝና ጊዜ የስኳር ህመም መታየት

• ሲጋራ ማጨስ እና አልኮል አብዝቶ መጠጣት

• ከፍተኛ ጭንቀት /ውጥረት/

• የስኳር ህመም ሳይታወቅ ሊቆይ ወይም ምንም ምልክት ላያሳይ ይችላል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት የታየባቸው ሰዎች የስኳር መጠናቸውን በደም ምርመራ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡

♡ የስኳር ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው

• ከፍተኛ የድካም ስሜት 

• ቶሎ ቶሎ መሽናት

• ከፍተኛ የውሀ ጥም

• የአይን ብዥታ

• ቶሎ የማይድን ቁስል

• የእጅ እና የእግር ጣቶች መደንዘዝ መለብለብ፡፡

♡ የስኳር መጠን መቆጣጠሪያ ዘዴዎች

● ጤናማ አመጋገብ

● ጣፋጭ ምግቦችን ማስወገድ

● ቅባታቸው ዝቅተኛ /አነስተኛ የሆኑ ምግቦችን መምረጥ

● ቅጠላቅጠል አትክልቶችን እና ፍራፍሬ መመገብ

● ያልተፈተጉ እህሎችን /ጥራጥሬዎችን ማዘውተር

● የአልኮል መጠን መቀነስ

● አለማጨስ

● በቂ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ

● የሰውነት ክብደትን መቀነስ/መቆጣጠር

● መድኃኒት በአግባቡ መውሰድ ይኸውም በመርፌ የሚሰጥ ኢንሱሊን ወይም በእንክብል የሚወሰድ መድኃኒት ሊሆን ይችላል፡፡

◇ ከስኳር ህመም ጋር የሚኖር ሰው በተጨማሪ ምን ማድረግ ይገባዋል

• የስኳር ህመም በተለያዩ የአካል ክፍሎቻችን ለምሳሌ አይን፣ ኩላሊት፣ ልብ ጭንቅላት….ላይ ተጓዳኝ ችግሮችን ሊፈጥር ይችላል፡፡ ስለዚህ ይህን ለመቀነስ ቅድመ ምርመራ /screening/ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

• ለእግር ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ

• ክብደትን መከታተል

• የአፍና የጥርስ ጤንነት መጠበቅ

• መድኃኒት ሀኪም ባዘዘው መሰረት መውሰድ እና

• መደበኛ ክትትል ከሀኪም ማግኘት ይኖርበታል፡፡

ከላይ መግቢያችን ላይ እንደገለፅነው ከሁለት ጎልማሶች አንዱ በስኳር ህመም መጠቃታቸውን ሳያውቁ ሊቆዩ ፣ለተወሳሰበ ህመመም ሊዳረጉ አልፎም ሊሞቱ ይችላሉ!!

   የስኳር ህመም ምርመራ በቀላሉ ሊደረግ የሚችል በመሆኑ ወደ ጤና ማዕከሎች ብቅ ብለው የጤናዎን ሁኔታ ያረጋግጡ! ከ ሀኪም ጋር ይመካከሩ! 


♡ የስኳር ህመም ምንድን ነው? ♡ የስኳር ህመም ምንድን ነው? Reviewed by Ayduwan on March 04, 2023 Rating: 5

No comments:

Powered by Blogger.