የልብ ድካም (Heart Disease)

 የልብ ድካም (Heart Disease)

☆☆ የልብ ድካም ማለት ልብ ሙሉ በሙሉ ስራዋን ማቆም ሳይሆን  በጤነኛ መንገድ  ተግባሯን ማከናወን አለመቻል ማለት ነው፡፡

《》ልብ ስትደክም የሚስተዋሉ #ምልክቶች

♧ የትንፋሽ መቆራረጥ

♧ ማታ ከተኙ በኋላ አየር በማጠር/ ከእንቅልፍ መነሳትና ንፋስን ፍለጋ ወደ መስኮት መሄድ፤መስኮት መክፈት

♧ የድካም ስሜት

♧ የእግር ማበጥ

♧ ሳል በተለይ ማታ ማታ፤አንዳንድ ጊዜ ሲያስለን ደም የቀላቀለ አክታ መኖር

♧ የልብ ትርታችን ከፍ ማለትና በስርዓት መምታት አለመቻል

♧ ስራ ስንሰራ ቶሎ መድከም

♧ ፈሳሽ በሰውነታችን ውስጥ ስለሚከማች የሰውነት ክብደት መጨመር

♧ ሆድ መነፋት

♧ የምግብ ፍላጎት መቀነስ

♧ የልባችን ትርታ /ምት ለሰው መታወቅ

♧ በልብና የግራ በኩል ደረትና ትከሻ ላይ የህመም ስሜት መሰማት

☆☆ የልብ ድካም ምክንያቶች

♤ የልብ #ደም #ቧንቧ #መጥበብ፡-ይህ በረጅም ጊዜ ውስጥ ስብ/ኮሌስትሮል በደም ስር ውስጥ እየተከማቸ ሲሄድ የልብ የደም ቧንቧ እየጠበበ ይሄዳል፡፡ ስብ ክምችቱ የደም ቧንቧው ድንገት ሊዘጋ ስለሚችል በዚህ ጊዜ ድንገት ሰዎችን ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡በተጨማርም የረጋው ደም ቧንቧውን በመዝጋት ከፍተኛ ህመም/ድንገተኛ የልብ ድካም ሊያደርስ ይችላል፡፡

♤ የደም ግፊት፡-የደም ግፊት ካለብን ልባችን የደም ቧንቧ ግፊት በመጨመር ለሰውነታችን ደም ለመርጨት ትልቅ ስራ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ከጊዜ በኋላ የልብ ጡንቻ በመወፈር በሂደት የልብ ግራ ክፍል እንዲሰፋ በማድረግ ልባችን ተግባሯን እንዳታከናወን ያደርጋታል፡፡

♤ የልብ በር ችግር፡-የልብ በር በመዘጋትና መከፈት ደም ልባችን ዉስጥ በመሄድ ለሌላው አካላችን ደም ለማሰራጨት ያገለግላል፡፡በመሆኑም የልብ በር ሲጎዳ ልብ ተግባሩን እንዳያከናውን በማድረግ በሂደት የልብ ድካምን ያስከትላል፡፡

♤ የልብ ጡንቻ ችግር፡- የልብ ጡንቻ በተለያዩ ኢንፌክሽኖች፤አልኮል አብዝቶ በመጠጣትና የተለያዩ መድሀኒቶችን በመውሰድ ሊታመም ይችላል፡፡ የጡንቻው አፈጣጠር አንዳንድ ሰዎች ለችግር ከተጋለጡ በቀላሉ እንዲጎዳ ያደርገዋል፡፡

♤ በአፈጣጠር የልብ አካላት ትክክል አለመሆን፡-የልብ አካላት አፈጣጠር ማለትም የልብ በር፤የደም ቧንቧና ሌሎችም በአፈጣጠር ትክክል ባለመሆኑ ልብ ስራዋን እንዳትፈጽም ያደርጋታል፡፡

♤ ሌሎች በሽታዎች እንደ የስኳር በሽታ፤ የታይሮይድን እጢ የሚያመርቱ ሆርሞኖች ብዛት፤ የረጋ ደም ከደም ቧንቧ ወደ ሳንባ የሚሄደውን በመዝጋት እና የደም ማነስ ለልብ ድካም ከሚያጋልጡ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ 

《》የልብ ጤንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉን መፍትሔዎች

◇ ሲጋራ አለማጨስ 

◇ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ፤ በተለይ በፍጥነት መራመድ፤ዋና፤ሩጫና ሌሎችንም በየቀኑ ለ30 ደቂቃና ቢያንስ በሳምንት ሶስት ቀን ማድረግ፡፡ ነገር ግን ወደ ደረት አከባቢና በግራ ትከሻችን ላይ ጠንከር ያለ የህመም ስሜት ከተሰማን ማቆም አለብን፡፡

◇ ቁመታችንና ክብደታችን ካልተመጣጠነ በተገቢው መልኩ ለማመጣጠን ክብደትን መቀነስ፤

◇ አትክልትና ፍራፍሬን ማዘወተር

◇ የምንጠቀመውን የጨው መጠን መቀነስ፤ጥሬ ስግ፤ጮማ፤እንቁላልና ቅቤን በሚገባ መቀነስ፡፡

◇ የደም ግፊትና ስኳር በሽታ ካለብን በመከታተል መቆጣጠር መቻል

የልብ ድካም (Heart Disease) የልብ ድካም (Heart Disease) Reviewed by Ayduwan on March 04, 2023 Rating: 5

No comments:

Powered by Blogger.