Results for March 4

የሐብሀብ የጤና ጥቅሞች

March 04, 2023

 የሐብሀብ 9 የጤና ጥቅሞች🍉

 ☆☆ ሃባብ የሚጣፍጥ፣ ጥምን የሚያረካ ፍራፍሬ ሲሆን በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅ እና በበጋ ወራት የሚዘወተር ነው ።

     👉 በጣም ከፍተኛ የውሃ ይዘት ያለው ሲሆን እና እንደ ሊኮፔን ፣ ሲቱርሊን እና ቫይታሚን ኤ እና ሲ ያሉ ጠቃሚ ንጥረነገሮችም ይዟል።

👉 ጥናቶች እንደሚያሳዩት ይህ ጣፋጭ ፍራፍሬ ብዙ የጤና ጥቅሞች ሲኖሩት ከእነሱም ውስጥ ዘጠኙን እናያለን ። 

1. የሰውነት እርጥበት እንዲጠበቅ ይረዳል

🍉 ሃባብ ከፍተኛ የውሃ ይዘት ያለዉ ፍራፍሬ ስለሆነ ሰውነታችን እርጥበት እንዲኖረው ያደርጋል - ይህም

አጠቃላይ ጤናዎን ይደግፋል - እንዲሁም ሙሉ ስሜት እንዲሰማዎት ያደርጋል።

2. በንጥረ ነገሮች እና ጠቃሚ የእፅዋት ውህዶች የተሞላ ነው

🍉 ሐብሀብ ከፍተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ኤ እና ሲን ጨምሮ በርካታ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል። እንደ ሊኮፔን

እና ኩኩሪቢታሲን ኢ ያሉ ፀረ-ባክቴሪያዎችንም ይሰጣል።

3. የፀረ-ካንሰር ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል

🍉 የጥናት ውጤቶቹ እንደሚያሳዩት ፣በሃባብ ውስጥ ያለ ላይኮፔን የተባለ ንጥረ ነገር አወሳሰድ ለአንዳንድ የካንሰር አይነቶች ለምሳሌ እንደ

ፕሮስቴት እና ኮሎሬክታል ካንሰሮች ተጋላጭነትን ሊቀንስ ይችላል።

 ሊኮፔን ካንሰርን የሚከላከለው በካንሰር ምክኒያት የሚፈጠረውን የበዛ የሕዋስ ክፍፍል መቆጣጠር እንዲቻል በማድረግ እና ሰውነትዎ የተበላሹ ህዋሳቶችን የሚያስወግድበትን ሂደት በመጨመር ነው።

4. የልብ ጤናን ያሻሽላል 

🍉 በሐብሀብ ውስጥ የሚገኙት ሊኮፔን እና ሲትሩሊን የታባሉት ንጥረነገሮች የደም ግፊትን እና ኮሌስትሮልን በመቀነስ የልብ ጤናን ይደግፋሉ ።

5. እብጠትን እና የኦክሳይድ ውጥረትን ሊቀንስ ይችላል።

🍉 አንድ ጥናት እንዳረጋገጠው በሐብሀብ ውስጥ የሚገኙት አንቲኦክሲዳንትስ፣ ሊኮፔን እና ቫይታሚን ሲ ጥምረት እብጠትን እና የኦክሳይድ ጉዳትን ለመቀነስ ይረዳል።

6. የዐይን መድከምን ለመከላከል ይረዳል

🍉 በሐብሀብ ውስጥ ያለው ሊኮፔን ይተባለው ንጥረነገር በፀረ-ኦክሲዳንት እና ፀረ-ብግነት ባህሪያቱ ምክንያት ከእድሜ ጋር የተያያዘ የዐይን መድከምን ለመከላከል ይረዳል።

7. የጡንቻ ህመምን ያስታግሳል

🍉 በሐብሀብ ውስጥ ያለው ሲትሩሊን ( citrulline) የተባለ ንጥረ ነገር የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ለማሻሻል እና የጡንቻ ህመምን ለመቀነስ ይረዳል።

8. የቆዳ ጤናን ይጠብቃል።

🍉 በሐብሀብ ውስጥ የሚገኙት ቫይታሚን ኤ እና ሲ ለቆዳ ጤንነት እጅግ ጠቃሚ ናቸው።

9. የምግብ መፈጨትን ሊያሻሽል ይችላል

🍉 ሃሐብሀ ብዙ ውሃ እና አነስተኛ መጠን ያለው ፋይበር ይይዛል፣ ሁለቱም ለጤናማ የምግብ መፈጨት ኡደት በጣም አስፈላጊ ናቸው።

 ይህም መደበኛ የአንጀት እንቅስቃሴን በመደገፍ የምግብ መፈጨትን ጤንነትን ሊረዳ ይችላል።


የሐብሀብ የጤና ጥቅሞች የሐብሀብ  የጤና ጥቅሞች Reviewed by Ayduwan on March 04, 2023 Rating: 5

♡ የስኳር ህመም ምንድን ነው?

March 04, 2023

  


♡ የስኳር ህመም ምንድን ነው?

የስኳር ህመም በደማችን ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከተገቢው በላይ መጨመር ሲሆን የሚከሰተውም ቆሽት የተባለው የሰውነት ክፍል ኢንሱሊን /Insulin/ የተባለውን ሆርሞን በበቂ ወይም ጭራሹን ማመንጨት ሲያቅተው ወይም የተመረተውን ኢንሱሊን በአግባቡ መጠቀም መስራት ሲያቅተው ነው፡፡

የስኳር ህመም ማንን ይይዛል?

• የስኳር ህመም እድሜ፣ ብሄር፣ ፆታ፣ የኑሮ ደረጃ ሳይል በሁሉም ሰው ሊከሰት የሚችል ህመም ነው፡፡

♡ ለስኳር ህመም ይበልጥ ተጋላጭ ማን ነው?

• የዕድሜ መጨመር /መግፋት

• ከመጠን ያለፈ ውፍረት /

• በቅርብ ቤተሰብ የስኳር ህመም መኖር

• ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ

• ከዚህ ቀደም በእርግዝና ጊዜ የስኳር ህመም መታየት

• ሲጋራ ማጨስ እና አልኮል አብዝቶ መጠጣት

• ከፍተኛ ጭንቀት /ውጥረት/

• የስኳር ህመም ሳይታወቅ ሊቆይ ወይም ምንም ምልክት ላያሳይ ይችላል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት የታየባቸው ሰዎች የስኳር መጠናቸውን በደም ምርመራ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡

♡ የስኳር ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው

• ከፍተኛ የድካም ስሜት 

• ቶሎ ቶሎ መሽናት

• ከፍተኛ የውሀ ጥም

• የአይን ብዥታ

• ቶሎ የማይድን ቁስል

• የእጅ እና የእግር ጣቶች መደንዘዝ መለብለብ፡፡

♡ የስኳር መጠን መቆጣጠሪያ ዘዴዎች

● ጤናማ አመጋገብ

● ጣፋጭ ምግቦችን ማስወገድ

● ቅባታቸው ዝቅተኛ /አነስተኛ የሆኑ ምግቦችን መምረጥ

● ቅጠላቅጠል አትክልቶችን እና ፍራፍሬ መመገብ

● ያልተፈተጉ እህሎችን /ጥራጥሬዎችን ማዘውተር

● የአልኮል መጠን መቀነስ

● አለማጨስ

● በቂ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ

● የሰውነት ክብደትን መቀነስ/መቆጣጠር

● መድኃኒት በአግባቡ መውሰድ ይኸውም በመርፌ የሚሰጥ ኢንሱሊን ወይም በእንክብል የሚወሰድ መድኃኒት ሊሆን ይችላል፡፡

◇ ከስኳር ህመም ጋር የሚኖር ሰው በተጨማሪ ምን ማድረግ ይገባዋል

• የስኳር ህመም በተለያዩ የአካል ክፍሎቻችን ለምሳሌ አይን፣ ኩላሊት፣ ልብ ጭንቅላት….ላይ ተጓዳኝ ችግሮችን ሊፈጥር ይችላል፡፡ ስለዚህ ይህን ለመቀነስ ቅድመ ምርመራ /screening/ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

• ለእግር ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ

• ክብደትን መከታተል

• የአፍና የጥርስ ጤንነት መጠበቅ

• መድኃኒት ሀኪም ባዘዘው መሰረት መውሰድ እና

• መደበኛ ክትትል ከሀኪም ማግኘት ይኖርበታል፡፡

ከላይ መግቢያችን ላይ እንደገለፅነው ከሁለት ጎልማሶች አንዱ በስኳር ህመም መጠቃታቸውን ሳያውቁ ሊቆዩ ፣ለተወሳሰበ ህመመም ሊዳረጉ አልፎም ሊሞቱ ይችላሉ!!

   የስኳር ህመም ምርመራ በቀላሉ ሊደረግ የሚችል በመሆኑ ወደ ጤና ማዕከሎች ብቅ ብለው የጤናዎን ሁኔታ ያረጋግጡ! ከ ሀኪም ጋር ይመካከሩ! 


♡ የስኳር ህመም ምንድን ነው? ♡ የስኳር ህመም ምንድን ነው? Reviewed by Ayduwan on March 04, 2023 Rating: 5

የተረከዝ_ህመም መንስኤዎች አሳሳቢ ምልክቶቹ እና መፍትሄዎቹ!

March 04, 2023

 የተረከዝ_ህመም መንስኤዎች አሳሳቢ ምልክቶቹ እና መፍትሄዎቹ!

♧ የተረከዝ ህመም መንስኤዎች ምንድን ናቸው?

በአብዛኛው ጊዜ የተረከዝ ህመም በታችኛው ወይም የውስጥ ተረከዝ እና በኋለኛው የተረከዝ ክፍል ላይ የሚከሰት ችግር ነው፡፡

♧ ዋነኛ ከሚባሉት የተረከዝ ህመም መንስኤዎች ውስጥ

- የተረከዝ ጅማት መቆጣት (Plantar Fasciitis)

- የተረከዝ አካባቢ የሚገኙ ነርቮች መቋጠር ችግር

- የቋንጃ ጅማት መቆጣት (Achilles Tendon Tendinitis)

- የቋንጃ ጅማት መደደር (Archillus ) Tendon Tendinopathy) 

- የተረከዝ አጥንት አጥንት አካባቢ ችግር 

- ሌሎች የውስጥ ደዌ ችግሮች ሲሆኑ ሌሎችም ተመሳሳይ ችግሮች መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

♤ የተረከዝ ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

- እንቅቃሴ ለመጀመር ሲታሰብ (ጠዋት ከእንቅልፍ ሲነሱ ወይም ከተቀመጡበት ለመነሳት ሲሞከር) የሚፈጠር ከባድ ህመም

- ከተወሰኑ ዕርምጃዎች በኋላ ህመም መቀነስ

- ረጅም ጊዜ ሲቆም ወይም ሲራመድ ከባድ ህመም መኖር

- የማቃጠል ወይም የመጠዝጠዝ አይነት ህመም

- የተረከዝ የጀርባው ክፍል መቅላት፣ ማበጥ እና ስቃይ 

☆ አሳሳቢ የተረከዝ ህመም ምልክቶች

- ህመሙ በጣም ተደጋጋሚ ሲሆን

- ከመደበኛ እንቅስቃሴዎች መዛነፍ ሲያስከትል

- ከተረከዝ አልፎ በሌላ የእግር አካባቢ (ባት፣ ጭን ወይም የጀርባ ህመም ተያይዞ ሲያመጣ)

- ቀላል በሚባሉ ዕርምጃዎች ምንም ለውጥ ማምጣት ካልተቻለ

- እነኚህን የመሳሰሉ ለውጦች ስታዩ የተረከዝ ህመም አሳሳቢ ሊሆን ስለሚገባ በእነኝህ አይነት የህመም ምልክቶች ከተጠቁ የአጥንት ስፔሻሊስት ጋር መታየት ይኖርበታል፡፡

:- ለተረከዝ ህመም መፍትሄ ይኖረው ይሆን?

አዎ!

 የተረከዝ ህመም ሳይባባስ ህክምና ከተደረገለት ቀላል በሚባሉ መፍትሄዎች ለውጥ ያሳያሉ

:- ከፍተኛ ስቃይ ከተሰማዎት እግርዎትን ቀዝቀዝ ባለ ውሀ ውስጥ ለጥቂት ደቂቃዎች ይዘፍዝፉ

:- ቀላል በሚባል የውስጥ እግር እሽታ ወይም ማሳጅ ማድረግ 

:- የውስጥ እግር ጅማ ማርዘሚያ ቀላል ስፖርቶችን ማድረግ

:- የውስጥ እግር ጅማት ማርዘሚያ ቀላል ስፖርቶችን ማድረግ 

:- የውስጥ ሶል ምቾት ያላቸው ጫማዎችን መጠቀም

:- የቀን ተቀን እንቅስቃሴን የተመጣጠነ ማድረግ

- እነዚህን የመሳሰሉ የግል ዕርዳታ የህክምና አማራጮችን ተጠቅመው ለውጥ ከላዩ አስፈላጊ ምርመራ ማድረግ ስለሚገባዎ አቅራቢዎ ወዳለ የጤና ተቋም ጎራ ብለው ተገቢውን ህክምና ያድርጉ፡፡


የተረከዝ_ህመም መንስኤዎች አሳሳቢ ምልክቶቹ እና መፍትሄዎቹ! የተረከዝ_ህመም መንስኤዎች አሳሳቢ ምልክቶቹ እና  መፍትሄዎቹ! Reviewed by Ayduwan on March 04, 2023 Rating: 5

የሚጥል በሽታ (Epilepsy; ኤፕለፕሲ)

March 02, 2023

 የሚጥል በሽታ (Epilepsy; ኤፕለፕሲ)

አጠቃላይ እይታ

✍️የሚጥል በሽታ (ኤፕለፕሲ) የረዥም ጊዜ (ሥር የሰደደ) ተላላፊ ያልሆነ የነርቭ (የአንጎል) በሽታ ሲሆን፣ በተጎዱ የአንጎል ሴሎች በሚፈጠር ያልተለመደ የአንጎል የኤሌክትሪክ ንዝረት ጊዜያዊ የነርቭ ሥርዓት መታወክ  ምክንያት ተደጋጋሚ የአንጎል መናድ (epileptic seizures) ያስከትላል

ክስተቱም ከጥቂት ሴኮንዶች እስከ 3 ደቂቃዎች የሚቆይ መፍዘዝ፣ ራስን መሳት፣ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ማንቀጥቀጥ ፣ የጡንቻ መገታተር ብሎም ታማሚው እንዲወድቅ ያደረጋል። አንድ ሰዉ የሚጥል በሽታ አለዉ ተብሎ የሚወሰነዉ በ 24 ሰዓታት ልዩነት ቢያንስ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ያልተቀሰቀሱ የሚጥል መናድ  (unprovoked seizures) ተደጋግሞ ሲከሰት ነዉ።

የሚጥል በሽታ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ወደ 50 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የሚጥል በሽታ አለባቸው፡፡ የሚጥል በሽታ ያለባቸው ሰዎች ወደ 80% የሚጠጉት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ውስጥ ይኖራሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ከ1000 ሰዎች መካከል 5 ሰዎች ወይም ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሰዎች የሚጥል በሽታ እንዳለባቸው ይገመታል።

የሚጥል በሽታ በንክኪ፣ በምራቅ፣ ህመምተኛውን በመርዳት አይተላለፍም፡፡

የሚጥል በሽታ በፈጣሪ ቁጣ፣ እርግማን ወይም እርኩስ መንፈስ የሚመጣ አይደለም፡፡ ስለዚህ የሚጥል በሽታ ያለባቸው ሰዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ማግለልና አድልኦ ማድረግ ተገቢ አይደለም።

 ✋የሚጥል በሽታ መንስዔዎች

የሚጥል በሽታ ካለባቸው ግማሽ ያህሉ ውስጥ መንስዔው  እስካሁን አይታወቅም ፡፡ ለሚጥል በሽታ ከሚያጋልጡ መንስዔዎች  መካከል ጥቂቶቹ  የሚከተሉትን ያካትታሉ፡፡

🎯በቅድመ ወሊድ እንዲሁም በወሊድ ጊዜ በተራዘመና አስቸጋሪ ምጥ ወቅት በህፃኑ ላይ በሚደርስ የአንጎል ጉዳት   

🎯ተፈጥሮአዊ በሆነ የአንጎል  እክል 

🎯ከባድ የጭንቅላት ጉዳት

🎯የአንጎል ኢንፌክሽን ለምሳሌ ማጅራት ገትር 

🎯 የአንጎል ዕጢ 

🎯 ስትሮክ

🎯በዘር የሚመጣ 

የሚጥል በሽታ ምልክቶች

የሚጥል በሽታ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ።

👉 እስከ 3 ደቂቃዎች የሚቆይ ጠቅላላ የሰዉነት ማንቀጥቀጥ እና ከዚህ ጋር ተያይዞ ራስን መሳትና መውደቅ፣ ዓይን ወደላይ መስቀል፣ አረፋ መድፈቅ ፣ ላይ ላዩን መተንፈስ እና ሽንት ማምለጥ፡፡ ታማሚው ከነቃ በኋላ የሆነውን ነገር ለማወቅ እና ለማስታወስ ይሳነዋል፣ ራስ ምታትም ሊኖርው ይችላል። 

👉ኢፕለፕሲ በብዛት የሚጥል በሽታ በመባል የሚታወቅ ቢሆንም ሳይጥል የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡ 

·   በድንገት መደነጋገር፣ መፍዘዝ ፣ ግንዛቤ ማጣት፣ያለማስተዋል ማፍጠጥ

·   ሳያስቡ መራመድ፣የት እንዳሉ መርሳት   

·   ደጋግሞ አላማ የሌለው የእጅና የሰውነት እንቅስቃሴዎች ማሳየት ፡፡ ለምሳሌ ከንፈር መምጠጥ፣ ዕቃዎችን በተደጋጋሚ ማንሳት ወይም ልብሶችን መሳብ

🤚ለሚጥል በሽታ የሚደረጉ ምርመራዎች

የታማሚው የሕክምና ታሪክ ለሚጥል በሽታ ምርመራ መሠረት ነው። ሐኪሙ ስለህመሙ ክስተት ሙሉ መረጃ ይፈልጋል። የሚጥል በሽታ ያጋጠማቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ የሆነውን ስለማያስታውሱ፣ ክስተቱን ያዩ የቤተሰብ አባላት ወይም ሌሎች ሰዎች ለሐኪሙ ማስረዳት አለባቸው። 

በታማሚው የሕክምና ታሪክ ላይ በመመሥረት የሚከተሉት የምርመራ አይነቶች ሊታዘዙ ይችላሉ።

👉የደም ናሙና ምርመራዎች 

👉 ኤሌክትሮኢንሴፋሎግራፊ (ኢኢጂ፤ EEG) መደበኛ ወይም ያልተለመደ የአንጎል የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ያሳያል።

👉ኤምአርአይ (MRI) ወይም ሲቲ ስካን (CT scan) የአንጎል መዋቅራዊ እክሎችን፤  የአንጎል ዕጢ እና የአንጎል ጠባሳችን ሊያሳዩ ይችላሉ።

 የሚጥል በሽታ ሕክምና

የሚጥል በሽታ በሕክምና መቆጣጠር ይቻላል። አንዳንድ የሚጥል በሽታ ሙሉበሙሉ ባይድንም ከመቶ 70 እጅ በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶችን በተገቢው መንገድ በመጠቀም በቁጥጥር ስር ሊውል ይቻላል።

ከበሽታው በህክምና ጥሩ ለውጥ ለማግኘት በሐኪሙ ምክር መሰረት ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል።

 👍 ለሚጥል በሽታ ተጠቂ ግለሰቦች ጠቃሚ ምክሮች

👉በቂ እንቅልፍ ማግኘት፤አለመጨነቅ፡፡

👉ከአልኮል መጠጦችና እና ሌሎች አደንዛዥ እጾችን መጠቀመም መቆጠብ ህመሙ እነዳይቀሰቀስ ያደርጋል፡፡ 

👉 ለአደጋ ከሚያጋልጡ ቦታዎች ለምሳሌ ከእሳት እና ገደል አጠገብ፤ ከከባድ ማሽኖች መራቅ አለባቸው፡፡

👉በዋና ከመዝናናትና መኪና ከማሽከርከር መቆጠብ አለባቸው፡፡

👉  በሐኪም የታዘዙ መድሀኒቶችን ያለ ሐኪም እውቅና ማቋረጥ ለህመሙ ማገርሸትን ስለሚያስከትል መድሀኒቶችን ላለማቋረጥ ጥንቃቄ ማድረግ፡፡ 

🤚ለሚጥል በሽታ የመጀመሪያ ዕርዳታ አሰጣጥ

በሚጥል በሽታ ሳቢያ የማንቀጥቀጥና ሕሊናን የመሳት ሁኔታ ያጋጠመውን ሰው ለመርዳት የሚከተሉትን መንገዶች መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ 

👉በጎን በኩል እንዲተኙ መርዳት 

👉 በጭንቅላት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ትራስ ማንተራስ 

👉 አንገት አካባቢ የታሰረ ማንኛውም ዓይነት ልብስ ወይም ጌጥ ማላላት 

👉በአካባቢ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ቁሳቁሶችን ማስገድ 

👉ሰውዬው አደጋ ላይ ካልሆነ በቀር አስጨንቆ አለመያዝ

👉 አፉ ውስጥ ባዕድ ነገር አለማስገባት ወይም አፉን እንዲከፍት አለመታገል

👉መንፈራገጡ እስከሚያቆም ድረስ እና ሙሉ በሙሉ ንቁ እስኪሆን ድረስ ከሰውየው ጋር ይቆዩ

👉 ክብሪት ወይም ማንኛውንም አይነት ጭስ አለማሸተት

ውድ ቤተሰቦች ምልክቶችን ቀድሞ በመገንዘብ  በሽታው የመጣል ደረጃ ላይ ሳይደርስ ጥንቃቀቄ ማድረግ እና ሳይባባስ ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው::

የሚጥል በሽታ (Epilepsy; ኤፕለፕሲ) የሚጥል በሽታ (Epilepsy; ኤፕለፕሲ) Reviewed by Ayduwan on March 02, 2023 Rating: 5
Powered by Blogger.