ካሮትና አቮካዶን ጨምሮ ለአይናችን ጤና እና የእይታ ጥራት የሚረዱ ምግቦች

March 06, 2023

 ■ ካሮትና አቮካዶን ጨምሮ ለአይናችን ጤና እና የእይታ ጥራት የሚረዱ ምግቦች

ለዓይን ጥራት ከፍተኛ ጥቅም አለው በሚል ለምግብነት ከሚውሉት ውስጥ ካሮት ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዝ ብዙዎቻችን እናውቃለን።

ተመራማሪዎች ከሰሞኑ ባወጡት የጥናት ውጤት ደግሞ ከካሮት በተጨማሪ አትክትሎችን ጨምሮ በርካታ ምግቦች የአይናችንን የእይታ ጥራት እና ጤና ለመጠበቅ ጠቀሜታ አላቸው ብለዋል።

የዓይንን ጤንነት እና የእይታ ጥራት ለመጠበቅ የሚረዱ ምግቦችም፦

1.አቮካዶ

አቮካዶ ሉተን እና ዠያንቲን የተባሉ አንቲ ኦክሲደንት ንጥረ ነገሮችን በውስጡ የያዘ በመሆኑ በብርሃን ምክንያት በዓይናችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት የመከላከል አቅሙ ከፍ ያለ ነው ተብሏል።

በፈረንሳይ የተሰራ ጥናት እንዳመለከተው፥ ዠያንቲን የተባለው አንቲ ኦክሲደንት በዕድሜ ምክንያት የሚከሰት የእይታ ችግር፣ በደም ግፊት፣ ለከፍተኛ የብርሃን ጨረር በመጋለጥ እና በአመጋገብ ችግር በዓይናችን ላይ የሚከሰተውን የጤና ችግር ይከላከላል።

በተጨማሪም አቮካዶ ቫይታሚን ሲ በውስጡ በመያዙ አይናችን ጤነኛ ሆኖ አንዲቆይ እንደሚረዳም ነው ጥናቱ ያመለከተው።

2.እንቁላል

እንቁላል የዓይናችንን ጤና በመጠበቅ በኩል ያለው ጠቀሜታም ከፍተኛ መሆኑ ይነገርለታል።

የቫይታሚን ኤ ምንጭ የሆነው እንቁላል ለዓይን ጤንነት ጠቃሚ ነው የተባለ ሲሆን፥ ልክ አንደ አቮካዶ የእንቁላል አስኳልም ዠያንቲን የተባለው አንቲ ኦክሲደንት በውስጡ በመያዙ በብርሃን ጨረር ምክንያት በዓይን ላይ የሚከሰትን ጉዳት ለመከላከል ይረዳል።

3.ካሮት

ካሮት የዓይናችንን የእይታ ጥራት እንደሚጨምር ከዚህ በፊት ሲነገር የነበረ ሲሆን ፥ በዚህኛው ጥናት ማረጋገጫ ማግኘቱም ተነግሯል።

በቫይታሚን ኤ የበለፀገው ካሮት ቤታ ካሮቲን የተባለ ንጥረ ነገር በውስጡ በመያዙ የዓይናችን የእይታ ጥራት ከፍ ያለ እንዲሆን እንደሚያደርገው ጥናቱ አመልክቷል።

በጥናቱ ላይ እንደተመለከተው ቫይታሚን ኤ፣ ቤታ ካሮቲን፣ ቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ኤ፣ ዚንክ እና ኮፐር ንጥረ ነገሮችን የሚወስዱ ሰዎች ከአድሜ ጋር ተያይዞ ለሚከሰት የዓይን ችግር የመጋለጥ እድላቸው 25 በመቶ የቀነሰ መሆኑ ተረጋግጧል።

4.አረንጓዴ ሻይ

አረንጓዴ ሻይ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት የሚነገርነት ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ የሰውነትን ክብደት ለመቀነስና የአእምሮን የመስራት አቅም መጨመር ተጠቃሽ ሲሆኑ፥ ከዚህ በተጨማሪም ለዓይናችን ጤንነት ጠቃሚ መሆኑ ተነግሯል።

በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ ያሉት እንደ ቫይታሚን ሲ፣ ሉተን እና ዠያንቲን የተባሉ አንቲ ኦክሲደንቶች ካንሰርን፣ የልብ ህመምን እና የዓይን በሽታን ለመከላከል እንደሚረዱ ጥናቱ አመልክቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የሚገኘው ገሎካትቺን የተባለ ንጥረ ነገር ለዓይን ጤንነት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑንም ነው ጥናቱ ያመለከተው።


ካሮትና አቮካዶን ጨምሮ ለአይናችን ጤና እና የእይታ ጥራት የሚረዱ ምግቦች  ካሮትና አቮካዶን ጨምሮ ለአይናችን ጤና እና የእይታ ጥራት የሚረዱ ምግቦች Reviewed by Ayduwan on March 06, 2023 Rating: 5

የልብ ድካም (Heart Disease)

March 04, 2023

 የልብ ድካም (Heart Disease)

☆☆ የልብ ድካም ማለት ልብ ሙሉ በሙሉ ስራዋን ማቆም ሳይሆን  በጤነኛ መንገድ  ተግባሯን ማከናወን አለመቻል ማለት ነው፡፡

《》ልብ ስትደክም የሚስተዋሉ #ምልክቶች

♧ የትንፋሽ መቆራረጥ

♧ ማታ ከተኙ በኋላ አየር በማጠር/ ከእንቅልፍ መነሳትና ንፋስን ፍለጋ ወደ መስኮት መሄድ፤መስኮት መክፈት

♧ የድካም ስሜት

♧ የእግር ማበጥ

♧ ሳል በተለይ ማታ ማታ፤አንዳንድ ጊዜ ሲያስለን ደም የቀላቀለ አክታ መኖር

♧ የልብ ትርታችን ከፍ ማለትና በስርዓት መምታት አለመቻል

♧ ስራ ስንሰራ ቶሎ መድከም

♧ ፈሳሽ በሰውነታችን ውስጥ ስለሚከማች የሰውነት ክብደት መጨመር

♧ ሆድ መነፋት

♧ የምግብ ፍላጎት መቀነስ

♧ የልባችን ትርታ /ምት ለሰው መታወቅ

♧ በልብና የግራ በኩል ደረትና ትከሻ ላይ የህመም ስሜት መሰማት

☆☆ የልብ ድካም ምክንያቶች

♤ የልብ #ደም #ቧንቧ #መጥበብ፡-ይህ በረጅም ጊዜ ውስጥ ስብ/ኮሌስትሮል በደም ስር ውስጥ እየተከማቸ ሲሄድ የልብ የደም ቧንቧ እየጠበበ ይሄዳል፡፡ ስብ ክምችቱ የደም ቧንቧው ድንገት ሊዘጋ ስለሚችል በዚህ ጊዜ ድንገት ሰዎችን ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡በተጨማርም የረጋው ደም ቧንቧውን በመዝጋት ከፍተኛ ህመም/ድንገተኛ የልብ ድካም ሊያደርስ ይችላል፡፡

♤ የደም ግፊት፡-የደም ግፊት ካለብን ልባችን የደም ቧንቧ ግፊት በመጨመር ለሰውነታችን ደም ለመርጨት ትልቅ ስራ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ከጊዜ በኋላ የልብ ጡንቻ በመወፈር በሂደት የልብ ግራ ክፍል እንዲሰፋ በማድረግ ልባችን ተግባሯን እንዳታከናወን ያደርጋታል፡፡

♤ የልብ በር ችግር፡-የልብ በር በመዘጋትና መከፈት ደም ልባችን ዉስጥ በመሄድ ለሌላው አካላችን ደም ለማሰራጨት ያገለግላል፡፡በመሆኑም የልብ በር ሲጎዳ ልብ ተግባሩን እንዳያከናውን በማድረግ በሂደት የልብ ድካምን ያስከትላል፡፡

♤ የልብ ጡንቻ ችግር፡- የልብ ጡንቻ በተለያዩ ኢንፌክሽኖች፤አልኮል አብዝቶ በመጠጣትና የተለያዩ መድሀኒቶችን በመውሰድ ሊታመም ይችላል፡፡ የጡንቻው አፈጣጠር አንዳንድ ሰዎች ለችግር ከተጋለጡ በቀላሉ እንዲጎዳ ያደርገዋል፡፡

♤ በአፈጣጠር የልብ አካላት ትክክል አለመሆን፡-የልብ አካላት አፈጣጠር ማለትም የልብ በር፤የደም ቧንቧና ሌሎችም በአፈጣጠር ትክክል ባለመሆኑ ልብ ስራዋን እንዳትፈጽም ያደርጋታል፡፡

♤ ሌሎች በሽታዎች እንደ የስኳር በሽታ፤ የታይሮይድን እጢ የሚያመርቱ ሆርሞኖች ብዛት፤ የረጋ ደም ከደም ቧንቧ ወደ ሳንባ የሚሄደውን በመዝጋት እና የደም ማነስ ለልብ ድካም ከሚያጋልጡ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ 

《》የልብ ጤንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉን መፍትሔዎች

◇ ሲጋራ አለማጨስ 

◇ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ፤ በተለይ በፍጥነት መራመድ፤ዋና፤ሩጫና ሌሎችንም በየቀኑ ለ30 ደቂቃና ቢያንስ በሳምንት ሶስት ቀን ማድረግ፡፡ ነገር ግን ወደ ደረት አከባቢና በግራ ትከሻችን ላይ ጠንከር ያለ የህመም ስሜት ከተሰማን ማቆም አለብን፡፡

◇ ቁመታችንና ክብደታችን ካልተመጣጠነ በተገቢው መልኩ ለማመጣጠን ክብደትን መቀነስ፤

◇ አትክልትና ፍራፍሬን ማዘወተር

◇ የምንጠቀመውን የጨው መጠን መቀነስ፤ጥሬ ስግ፤ጮማ፤እንቁላልና ቅቤን በሚገባ መቀነስ፡፡

◇ የደም ግፊትና ስኳር በሽታ ካለብን በመከታተል መቆጣጠር መቻል

የልብ ድካም (Heart Disease) የልብ ድካም (Heart Disease) Reviewed by Ayduwan on March 04, 2023 Rating: 5

የጨጓራ ባክቴሪያ

March 04, 2023

 የጨጓራ ባክቴሪያ

:> የጨጓራ ባክቴሪያ ወይም ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ(Helicobacter pylori (H. pylori)) ወደ ሰውነታችን በመግባት የምግብ ትቦ ላይ እና  ጨጓራ ውስጥ መኖር የሚችል ነው፡፡ ይህ ባክቴሪያ ሳይታከም ከቆየ አልሰር/  ቁስለት በጨጓራ ላይ እና በትንሹ አንጀት የላይኛው ክፍል ላይ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ አለፈፍ ሲልም ካንሰርንም ሊያስከትል ይችላል፡፡

♧ በጨጓራ ባክቴሪያ መያዝ በብዙዎች ላይ የሚያጋጥም የተለመደ በሽታ ቢሆንም ባክቴሪያው አንዳንድ ሰዎች ላይ ምንም ምልክት የማያሳይ፣ የቁስለት ሁኔታም የማይፈጥር ቢሆንም ብዙዎችን ግን ለከፍተኛ ለሕመም ይዳርጋል፡፡

:> ባክቴሪው እንዴት ህመም ይፈጥራል?

◇ የጨጓራ ባክቴሪያ ወደ ሰውነት ከገባ በኋላ በጨጓራ ውስጣዊ አካል ላይ ጥቃት በመፈፀም ጨጓራችንን ተጋላጭ ያደርገዋል፤ ምክንያቱም ጨጓራችን ምግብ ለመፍጨት አሲድ ይጠቀማል፡፡ ይህ አሲድ በጨጓራ አካል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሚያደርገው የጨጓራ  ውስጣዊ አካል ነው፡፡ ይህ አካል ከተሸረሸረ ጨጓራችን ለአሲዱ የተጋለጠ ስለሚሆን ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ጉዳቱ የደም መፍሰስ ጨምሮ አካሉ እንዲቆስል፣ እንዲሁም የበላነው ምግብ እንዳይፈጭና እንዳይረጋ ሊያደርግ ይችላል፡፡

:> ይህ ባክቴሪያ ከየት ሊያገኘን ይችላል?

♤ የጨጓራ ባክቴሪያ ከምንበላው ምግብ፣ ከምንጠጣው ውኃና ከምንጠቀማቸው በባክቴሪው ከተበከሉ ቁሶች ሊያገኘን ይችላል፡፡ በሽታው አብዛኛውን ጊዜ ፅዳት በሚጎድልባቸው አካባቢዎች የሚከሰት ሲሆን ባክቴሪያው በምራቅ ንክኪና ባክቴሪያው ካለበት ሰው ጋር በሚኖር የፈሳሽ ንክኪ ሊተላለፍብን ይችላል፡፡ 

:> የጨጓራ ባክቴሪያ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

□ የሆድ መነፋት 

□ ግሳት

□ የረሃብ ስሜት አለመሰማት

□ ማቅለሽለሽ

□ ማስመለስ

□ ቁስለት ከተፈጠረብን በሆዳችን የላይኛው ክፍል የማቃጠልና

 የመደንዘዝ ስሜት

□ ያለምክንያት ክብደት መቀነስ ሊታዩ ይችላሉ፡፡

:> መቼ ወደ ህክምና መሄድ #ይኖርብናል? 

● የሰገራ መጥቆርና ደም መቀላቀል ካለ

● ለመተንፈስ መቸገር ካጋጠመን

● ያለስራ የመልፈስፈስና የድካም ስሜት ከተጫነን

● የቆዳ መገርጣትና ራስን የመሳት ሁኔታ ከታየብን

● የተፈጨ ቡና የመሰለ ነገር የሚያስመልሰን ከሆነ

● ከባድ የሆድ ህመም ካለን የጨጓራ ባክቴሪያ ሊሆን ስለሚችል መታየት አለብን፡፡

:> ምርመራ

○ የኋላ ታሪክን በመጠየቅ

○ ትንፋሽ ምርመራ

○ የኢንዶስኮፒ ምርመራ

:> ሕክምና

○ ጸረ - በክቴሪያ መድኃኒቶች

○ በጨጓራ ውስጥ አሲድ የሚረጩትን ጥቃቅን ቧንቧዎች በመዝጋት አሲድ የሚቀንሱ መድኃኒቶችን

○ የአመጋገብ ስርአት ማስተካከለል ይካተቱበታል፡፡

ለበለጠ በአቅራቢያ የሚገኝ የህክምና ተቋም ይሂዱ::

የጨጓራ ባክቴሪያ የጨጓራ ባክቴሪያ Reviewed by Ayduwan on March 04, 2023 Rating: 5

ስትሮክ

March 04, 2023

 ስትሮክ

ስትሮክ_ምንድን_ነው?


🖋 የራስ ቅል (ጭንቅላት)ውስጥ ደም ሲፈስ

🖋 ወደ ጭንቅላት ውስጥ የጓጎለ ደም ሲገባ

🖋 ወደ ጭቅላት የሚገባው ደም ሲቋረጥ ነው።

እንደ አጠቃላይ ስትሮክ ማለት ከላይ በተጠቀሱት ምክናየት አንጎል ሲጠቃ ነው።

《》ዋና_ዋና_የስትሮክ_ምልክቶች_ምን_ምን_ናቸው?

1. የእጅ፡ የእግርና የፊት መደንዘዝና መስነፍ

2. እይታን ማጣት

3. መናገር አለመቻል

4. ሌሎች የተናገሩንንም መረዳት አለመቻል

5. ድንገተኛና ከባድ የራስ ምታት

6. የሰውነትን ሚዛን መጠበቅ አለመቻል

《》ስትሮክን_መከላከል_ይቻላል?

♧ አዎ መከላከል ይቻላል።

◇ ለስትሮክ_የሚያጋልጡ_ነገሮች

1. ከፍተኛ የደም ግፊት

2. የልብ ችግር(ሁሉም አይደለም)

3. ከቁጥጥር ያለፈ የስኳር በሽታ

4. የኰሌስትሮል መጠን መጨመር

5. ማጤስ

6. መጡኑ የጨመረ የአልኮል መጠጥ

7. ውፍረት

8. ጭንቅላትንና ልብን የሚመግቡ የደም ቱቦዎች ላይ ችግር ካለ።

9. ወንድ መሆን፡ እድሜ ከ65በላይ ከሆነ፡ በቤተሰብ ካለ የመጠቃት እድል ከሌሎች አኳያ ይጨምራል።

¤ አስታውሱ

በህይዎተዎ ሳያውቁት አንድ ጊዜም ይሁን ከዚያ በላይ እራሰዎን ስተው የመውደቅ አጋጣሚ ከገጠመዎት በስትሮክ የመመታት እድሉ ሊኖረዎት ስለሚችል እራሰዎን ለሀኪም ያሳዩ

ስትሮክ ስትሮክ Reviewed by Ayduwan on March 04, 2023 Rating: 5

የሐብሀብ የጤና ጥቅሞች

March 04, 2023

 የሐብሀብ 9 የጤና ጥቅሞች🍉

 ☆☆ ሃባብ የሚጣፍጥ፣ ጥምን የሚያረካ ፍራፍሬ ሲሆን በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅ እና በበጋ ወራት የሚዘወተር ነው ።

     👉 በጣም ከፍተኛ የውሃ ይዘት ያለው ሲሆን እና እንደ ሊኮፔን ፣ ሲቱርሊን እና ቫይታሚን ኤ እና ሲ ያሉ ጠቃሚ ንጥረነገሮችም ይዟል።

👉 ጥናቶች እንደሚያሳዩት ይህ ጣፋጭ ፍራፍሬ ብዙ የጤና ጥቅሞች ሲኖሩት ከእነሱም ውስጥ ዘጠኙን እናያለን ። 

1. የሰውነት እርጥበት እንዲጠበቅ ይረዳል

🍉 ሃባብ ከፍተኛ የውሃ ይዘት ያለዉ ፍራፍሬ ስለሆነ ሰውነታችን እርጥበት እንዲኖረው ያደርጋል - ይህም

አጠቃላይ ጤናዎን ይደግፋል - እንዲሁም ሙሉ ስሜት እንዲሰማዎት ያደርጋል።

2. በንጥረ ነገሮች እና ጠቃሚ የእፅዋት ውህዶች የተሞላ ነው

🍉 ሐብሀብ ከፍተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ኤ እና ሲን ጨምሮ በርካታ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል። እንደ ሊኮፔን

እና ኩኩሪቢታሲን ኢ ያሉ ፀረ-ባክቴሪያዎችንም ይሰጣል።

3. የፀረ-ካንሰር ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል

🍉 የጥናት ውጤቶቹ እንደሚያሳዩት ፣በሃባብ ውስጥ ያለ ላይኮፔን የተባለ ንጥረ ነገር አወሳሰድ ለአንዳንድ የካንሰር አይነቶች ለምሳሌ እንደ

ፕሮስቴት እና ኮሎሬክታል ካንሰሮች ተጋላጭነትን ሊቀንስ ይችላል።

 ሊኮፔን ካንሰርን የሚከላከለው በካንሰር ምክኒያት የሚፈጠረውን የበዛ የሕዋስ ክፍፍል መቆጣጠር እንዲቻል በማድረግ እና ሰውነትዎ የተበላሹ ህዋሳቶችን የሚያስወግድበትን ሂደት በመጨመር ነው።

4. የልብ ጤናን ያሻሽላል 

🍉 በሐብሀብ ውስጥ የሚገኙት ሊኮፔን እና ሲትሩሊን የታባሉት ንጥረነገሮች የደም ግፊትን እና ኮሌስትሮልን በመቀነስ የልብ ጤናን ይደግፋሉ ።

5. እብጠትን እና የኦክሳይድ ውጥረትን ሊቀንስ ይችላል።

🍉 አንድ ጥናት እንዳረጋገጠው በሐብሀብ ውስጥ የሚገኙት አንቲኦክሲዳንትስ፣ ሊኮፔን እና ቫይታሚን ሲ ጥምረት እብጠትን እና የኦክሳይድ ጉዳትን ለመቀነስ ይረዳል።

6. የዐይን መድከምን ለመከላከል ይረዳል

🍉 በሐብሀብ ውስጥ ያለው ሊኮፔን ይተባለው ንጥረነገር በፀረ-ኦክሲዳንት እና ፀረ-ብግነት ባህሪያቱ ምክንያት ከእድሜ ጋር የተያያዘ የዐይን መድከምን ለመከላከል ይረዳል።

7. የጡንቻ ህመምን ያስታግሳል

🍉 በሐብሀብ ውስጥ ያለው ሲትሩሊን ( citrulline) የተባለ ንጥረ ነገር የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ለማሻሻል እና የጡንቻ ህመምን ለመቀነስ ይረዳል።

8. የቆዳ ጤናን ይጠብቃል።

🍉 በሐብሀብ ውስጥ የሚገኙት ቫይታሚን ኤ እና ሲ ለቆዳ ጤንነት እጅግ ጠቃሚ ናቸው።

9. የምግብ መፈጨትን ሊያሻሽል ይችላል

🍉 ሃሐብሀ ብዙ ውሃ እና አነስተኛ መጠን ያለው ፋይበር ይይዛል፣ ሁለቱም ለጤናማ የምግብ መፈጨት ኡደት በጣም አስፈላጊ ናቸው።

 ይህም መደበኛ የአንጀት እንቅስቃሴን በመደገፍ የምግብ መፈጨትን ጤንነትን ሊረዳ ይችላል።


የሐብሀብ የጤና ጥቅሞች የሐብሀብ  የጤና ጥቅሞች Reviewed by Ayduwan on March 04, 2023 Rating: 5

♡ የስኳር ህመም ምንድን ነው?

March 04, 2023

  


♡ የስኳር ህመም ምንድን ነው?

የስኳር ህመም በደማችን ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከተገቢው በላይ መጨመር ሲሆን የሚከሰተውም ቆሽት የተባለው የሰውነት ክፍል ኢንሱሊን /Insulin/ የተባለውን ሆርሞን በበቂ ወይም ጭራሹን ማመንጨት ሲያቅተው ወይም የተመረተውን ኢንሱሊን በአግባቡ መጠቀም መስራት ሲያቅተው ነው፡፡

የስኳር ህመም ማንን ይይዛል?

• የስኳር ህመም እድሜ፣ ብሄር፣ ፆታ፣ የኑሮ ደረጃ ሳይል በሁሉም ሰው ሊከሰት የሚችል ህመም ነው፡፡

♡ ለስኳር ህመም ይበልጥ ተጋላጭ ማን ነው?

• የዕድሜ መጨመር /መግፋት

• ከመጠን ያለፈ ውፍረት /

• በቅርብ ቤተሰብ የስኳር ህመም መኖር

• ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ

• ከዚህ ቀደም በእርግዝና ጊዜ የስኳር ህመም መታየት

• ሲጋራ ማጨስ እና አልኮል አብዝቶ መጠጣት

• ከፍተኛ ጭንቀት /ውጥረት/

• የስኳር ህመም ሳይታወቅ ሊቆይ ወይም ምንም ምልክት ላያሳይ ይችላል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት የታየባቸው ሰዎች የስኳር መጠናቸውን በደም ምርመራ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡

♡ የስኳር ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው

• ከፍተኛ የድካም ስሜት 

• ቶሎ ቶሎ መሽናት

• ከፍተኛ የውሀ ጥም

• የአይን ብዥታ

• ቶሎ የማይድን ቁስል

• የእጅ እና የእግር ጣቶች መደንዘዝ መለብለብ፡፡

♡ የስኳር መጠን መቆጣጠሪያ ዘዴዎች

● ጤናማ አመጋገብ

● ጣፋጭ ምግቦችን ማስወገድ

● ቅባታቸው ዝቅተኛ /አነስተኛ የሆኑ ምግቦችን መምረጥ

● ቅጠላቅጠል አትክልቶችን እና ፍራፍሬ መመገብ

● ያልተፈተጉ እህሎችን /ጥራጥሬዎችን ማዘውተር

● የአልኮል መጠን መቀነስ

● አለማጨስ

● በቂ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ

● የሰውነት ክብደትን መቀነስ/መቆጣጠር

● መድኃኒት በአግባቡ መውሰድ ይኸውም በመርፌ የሚሰጥ ኢንሱሊን ወይም በእንክብል የሚወሰድ መድኃኒት ሊሆን ይችላል፡፡

◇ ከስኳር ህመም ጋር የሚኖር ሰው በተጨማሪ ምን ማድረግ ይገባዋል

• የስኳር ህመም በተለያዩ የአካል ክፍሎቻችን ለምሳሌ አይን፣ ኩላሊት፣ ልብ ጭንቅላት….ላይ ተጓዳኝ ችግሮችን ሊፈጥር ይችላል፡፡ ስለዚህ ይህን ለመቀነስ ቅድመ ምርመራ /screening/ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

• ለእግር ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ

• ክብደትን መከታተል

• የአፍና የጥርስ ጤንነት መጠበቅ

• መድኃኒት ሀኪም ባዘዘው መሰረት መውሰድ እና

• መደበኛ ክትትል ከሀኪም ማግኘት ይኖርበታል፡፡

ከላይ መግቢያችን ላይ እንደገለፅነው ከሁለት ጎልማሶች አንዱ በስኳር ህመም መጠቃታቸውን ሳያውቁ ሊቆዩ ፣ለተወሳሰበ ህመመም ሊዳረጉ አልፎም ሊሞቱ ይችላሉ!!

   የስኳር ህመም ምርመራ በቀላሉ ሊደረግ የሚችል በመሆኑ ወደ ጤና ማዕከሎች ብቅ ብለው የጤናዎን ሁኔታ ያረጋግጡ! ከ ሀኪም ጋር ይመካከሩ! 


♡ የስኳር ህመም ምንድን ነው? ♡ የስኳር ህመም ምንድን ነው? Reviewed by Ayduwan on March 04, 2023 Rating: 5

የተረከዝ_ህመም መንስኤዎች አሳሳቢ ምልክቶቹ እና መፍትሄዎቹ!

March 04, 2023

 የተረከዝ_ህመም መንስኤዎች አሳሳቢ ምልክቶቹ እና መፍትሄዎቹ!

♧ የተረከዝ ህመም መንስኤዎች ምንድን ናቸው?

በአብዛኛው ጊዜ የተረከዝ ህመም በታችኛው ወይም የውስጥ ተረከዝ እና በኋለኛው የተረከዝ ክፍል ላይ የሚከሰት ችግር ነው፡፡

♧ ዋነኛ ከሚባሉት የተረከዝ ህመም መንስኤዎች ውስጥ

- የተረከዝ ጅማት መቆጣት (Plantar Fasciitis)

- የተረከዝ አካባቢ የሚገኙ ነርቮች መቋጠር ችግር

- የቋንጃ ጅማት መቆጣት (Achilles Tendon Tendinitis)

- የቋንጃ ጅማት መደደር (Archillus ) Tendon Tendinopathy) 

- የተረከዝ አጥንት አጥንት አካባቢ ችግር 

- ሌሎች የውስጥ ደዌ ችግሮች ሲሆኑ ሌሎችም ተመሳሳይ ችግሮች መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

♤ የተረከዝ ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

- እንቅቃሴ ለመጀመር ሲታሰብ (ጠዋት ከእንቅልፍ ሲነሱ ወይም ከተቀመጡበት ለመነሳት ሲሞከር) የሚፈጠር ከባድ ህመም

- ከተወሰኑ ዕርምጃዎች በኋላ ህመም መቀነስ

- ረጅም ጊዜ ሲቆም ወይም ሲራመድ ከባድ ህመም መኖር

- የማቃጠል ወይም የመጠዝጠዝ አይነት ህመም

- የተረከዝ የጀርባው ክፍል መቅላት፣ ማበጥ እና ስቃይ 

☆ አሳሳቢ የተረከዝ ህመም ምልክቶች

- ህመሙ በጣም ተደጋጋሚ ሲሆን

- ከመደበኛ እንቅስቃሴዎች መዛነፍ ሲያስከትል

- ከተረከዝ አልፎ በሌላ የእግር አካባቢ (ባት፣ ጭን ወይም የጀርባ ህመም ተያይዞ ሲያመጣ)

- ቀላል በሚባሉ ዕርምጃዎች ምንም ለውጥ ማምጣት ካልተቻለ

- እነኚህን የመሳሰሉ ለውጦች ስታዩ የተረከዝ ህመም አሳሳቢ ሊሆን ስለሚገባ በእነኝህ አይነት የህመም ምልክቶች ከተጠቁ የአጥንት ስፔሻሊስት ጋር መታየት ይኖርበታል፡፡

:- ለተረከዝ ህመም መፍትሄ ይኖረው ይሆን?

አዎ!

 የተረከዝ ህመም ሳይባባስ ህክምና ከተደረገለት ቀላል በሚባሉ መፍትሄዎች ለውጥ ያሳያሉ

:- ከፍተኛ ስቃይ ከተሰማዎት እግርዎትን ቀዝቀዝ ባለ ውሀ ውስጥ ለጥቂት ደቂቃዎች ይዘፍዝፉ

:- ቀላል በሚባል የውስጥ እግር እሽታ ወይም ማሳጅ ማድረግ 

:- የውስጥ እግር ጅማ ማርዘሚያ ቀላል ስፖርቶችን ማድረግ

:- የውስጥ እግር ጅማት ማርዘሚያ ቀላል ስፖርቶችን ማድረግ 

:- የውስጥ ሶል ምቾት ያላቸው ጫማዎችን መጠቀም

:- የቀን ተቀን እንቅስቃሴን የተመጣጠነ ማድረግ

- እነዚህን የመሳሰሉ የግል ዕርዳታ የህክምና አማራጮችን ተጠቅመው ለውጥ ከላዩ አስፈላጊ ምርመራ ማድረግ ስለሚገባዎ አቅራቢዎ ወዳለ የጤና ተቋም ጎራ ብለው ተገቢውን ህክምና ያድርጉ፡፡


የተረከዝ_ህመም መንስኤዎች አሳሳቢ ምልክቶቹ እና መፍትሄዎቹ! የተረከዝ_ህመም መንስኤዎች አሳሳቢ ምልክቶቹ እና  መፍትሄዎቹ! Reviewed by Ayduwan on March 04, 2023 Rating: 5
Powered by Blogger.